Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 14:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ዳዊ​ትም ወደ በኣ​ል​ፐ​ራ​ሲን ወጣ፤ በዚ​ያም ዳዊት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መታ​ቸው። ዳዊ​ትም፥ “ውኃ እን​ዲ​ያ​ጠፋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶ​ቼን በእጄ አጠ​ፋ​ቸው” አለ። ስለ​ዚ​ህም የዚ​ያን ስፍራ ስም በኣ​ል​ፐ​ራ​ሲን ብለው ጠሩት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ በኣልፐራሲም ወጡ፤ በዚያም ድል አደረጋቸው። ዳዊትም፣ “የጐርፍ ውሃ ጥሶ በመውጣት እንደሚያፈራርስ ሁሉ እግዚአብሔርም ጠላቶቼን በእጄ አፈራረሳቸው” አለ፤ ከዚህ የተነሣም የዚያ ቦታ ስም “በኣልፐራሲም” ተባለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ወደ በኣል-ፐራሲምም ወጡ፥ በዚያም ዳዊት ድል ነሣቸው። ዳዊትም፦ “ግድቡን አፍርሶ እንደሚወጣ ጎርፍ እግዚአብሔር ጠላቶቼን በእጄ አፈረሳቸው” አለ። ስለዚህም የዚያን ስፍራ ስም በኣል-ፐራሲም ብለው ጠሩት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ስለዚህ ዳዊት ባዓልፈራጺም ተብሎ በሚጠራ ስፍራ በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ጥሎ ድል ካደረጋቸው በኋላ “የጠላትን ሠራዊት እንደ ጐርፍ ጥሼ እንዳልፍ እግዚአብሔር ረዳኝ” አለ፤ ከዚያም በኋላ ያ ስፍራ “ባዓልፈራጺም” ተብሎ ተጠራ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ወደ በኣልፐራሲምም ወጡ፤ በዚያም ዳዊት መታቸው። ዳዊትም “ውሃ እንዲያፈርስ እግዚአብሔር ጠላቶቼን በእጄ አፈረሳቸው፤” አለ። ስለዚህም የዚያን ስፍራ ስም “በኣልፐራሲም” ብለው ጠሩት።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 14:11
11 交叉引用  

ዳዊ​ትም ከላ​ይ​ኛው መጋ​ደያ መጣ፤ በዚ​ያም መታ​ቸ​ውና፥ “ውኃ እን​ደ​ሚ​ያ​ጠፋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶቼን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን በፊቴ አጠ​ፋ​ቸው” አለ። ስለ​ዚ​ህም የዚያ ስፍራ ስም “የላ​ይ​ኛው መጋ​ደያ” ተብሎ ተጠራ።


ዳዊ​ትም፥ “ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ልው​ጣን? በእ​ጄስ አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ህን?” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ውጣ” አለው።


አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በዚያ ተዉ፤ ዳዊ​ትም፥ “በእ​ሳት አቃ​ጥ​ሉ​አ​ቸው” ብሎ አዘዘ።


እንደ ወደደ አደ​ረ​ገ​ብኝ፤ በመ​ከ​ራም እዛ​ብ​ራ​ለሁ።


አም​ላኬ ንጉሤ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፥ ስም​ህ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዓለም አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ።


አቤቱ፥ ፍጥ​ረ​ትህ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፥ ጻድ​ቃ​ን​ህም ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል።


ኀያል ሆይ፥ በደም ግባ​ት​ህና በው​በ​ትህ፥ ሰይ​ፍ​ህን በወ​ገ​ብህ ታጠቅ።


ውኃ​ውም ተመ​ልሶ በኋ​ላ​ቸው ወደ ባሕር የገ​ቡ​ትን ሰረ​ገ​ሎ​ችን፥ ፈረ​ሰ​ኞ​ች​ንም፥ የፈ​ር​ዖ​ን​ንም ሠራ​ዊት ሁሉ ከደነ፤ ከመ​ጡ​ትም ሁሉ አንድ ስንኳ የቀረ የለም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በኃ​ጥ​ኣን ተራራ እንደ ነበረ ይነ​ሣል፤ በገ​ባ​ዖን ሸለ​ቆም ይኖ​ራል፤ ሥራ​ውን ማለት መራራ ሥራ​ውን በቍጣ ይሠ​ራል፤ ቍጣ​ውም ድን​ቅን ያደ​ር​ጋል፤ መር​ዙም ልዩ ነው።


ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት መታው፤ ወደቀም፤ አወዳደቁም ታላቅ ሆነ።”


跟着我们:

广告


广告