1 ዜና መዋዕል 13:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 የእግዚአብሔርንም ታቦት ከአሚናዳብ ቤት በተገኘ በአዲስ ሰረገላ ላይ አኖሩአት። ዖዛና ወንድሞቹም ሰረገላውን ይነዱ ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም7 የእግዚአብሔርንም ታቦት ከአሚናዳብ ቤት በአዲስ ሠረገላ ላይ አድርገው አመጡት፤ ሠረገላውን ይነዱ የነበሩትም ዖዛና አሒዮ ነበሩ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 የእግዚአብሔርንም ታቦት በአዲስ ሠረገላ ላይ ጫኑት፥ ከአሚናዳብም ቤት አመጡት፤ ዖዛና አሒዮም ሠረገላውን ይነዱ ነበር። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 የቃል ኪዳኑን ታቦት ከአቢናዳብ ቤት አውጥተው በአዲስ ሠረገላ ላይ ጫኑት፤ ዑዛና አሕዮም ሠረገላውን ይነዱ ነበር፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 የእግዚአብሔርንም ታቦት በአዲስ ሠረገላ ላይ ጫኑት፤ ከአሚናዳብም ቤት አመጡት፤ ዖዛና አሒዮም ሠረገላውን ይነዱ ነበር። 参见章节 |