Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 12:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 ደግ​ሞም በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ደስታ ሆኖ​አ​ልና እስከ ይሳ​ኮ​ርና እስከ ዛብ​ሎን እስከ ንፍ​ታ​ሌ​ምም ድረስ ለእ​ርሱ አቅ​ራ​ቢያ የነ​በሩ በአ​ህ​ያና በግ​መል በበ​ቅ​ሎና በበሬ ላይ እን​ጀ​ራና ዱቄት የበ​ለስ ጥፍ​ጥ​ፍና የዘ​ቢብ ዘለላ የወ​ይ​ንም ጠጅ፥ ዘይ​ትም በሬ​ዎ​ች​ንና በጎ​ች​ንም፥ ፍየ​ሎ​ች​ንም በብዙ አድ​ር​ገው ያመጡ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 እንዲሁም ሩቅ ከሆነው ከይሳኮር፣ ከዛብሎንና ከንፍታሌም አገር ሳይቀር ጎረቤቶቻቸው በአህያ፣ በግመል፣ በበቅሎና በበሬ ጭነው ምግብ አመጡላቸው፤ በእስራኤል ታላቅ ደስታ ስለ ሆነ ዱቄት፣ የበለስና የዘቢብ ጥፍጥፍ፣ የወይን ጠጅ፣ የወይራ ዘይት፣ የቀንድ ከብትና በጎች በገፍ ቀርበው ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ደግሞም በእስራኤል ዘንድ ደስታ ሆኖአልና ከይሳኮርና ከዛብሎን ከንፍታሌምም ድረስ በእርሱ አቅራቢያ የነበሩ በአህያና በግመል በበቅሎና በበሬ ላይ እንጀራ ዱቄት የበለስ ጥፍጥፍና የዘቢብ ዘለላ የወይንም ጠጅ ዘይትም በሬዎችንና በጎችንም በብዛት ያመጡ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 በስተ ሰሜን በኩል ካሉት ከይሳኮር፥ ከዛብሎንና ከንፍታሌም ነገዶች ሳይቀር ብዙ ሰዎች በአህያ፥ በግመል፥ በበቅሎና በበሬ ብዙ ምግብ፥ ዱቄት፥ በለስ፥ ዘቢብ፥ የወይን ጠጅና የወይራ ዘይት በመጫን ይዘው መጥተው ነበር፤ እንዲሁም ዐርደው የሚበሉአቸውን ብዙ የቀንድ ከብቶችና በጎችን ይዘው መጥተዋል፤ ይህም ሁሉ በመላው አገሪቱ ላይ የሚገኘው ሕዝብ የተሰማውን ደስታ የሚገልጥ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ደግሞም በእስራኤል ዘንድ ደስታ ሆኖአልና እስከ ይሳኮርና እስከ ዛብሎን እስከ ንፍታሌምም ድረስ ለእርሱ አቅራቢያ የነበሩ በአህያና በግመል በበቅሎና በበሬ ላይ እንጀራና ዱቄት የበለስ ጥፍጥፍና የዘቢብ ዘለላ የወይንም ጠጅ ዘይትም በሬዎችንና በጎችንም በብዙ አድርገው ያመጡ ነበር።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 12:40
14 交叉引用  

ዳዊ​ትም ከተ​ራ​ራው ራስ ጥቂት እልፍ አለ። እነ​ሆም፥ የሜ​ም​ፌ​ቡ​ስቴ አገ​ል​ጋይ ሲባ ሁለት መቶ እን​ጀራ፥ አንድ መቶም ዘለላ ዘቢብ፥ አንድ መቶም ተምር፥ አንድ አቁ​ማ​ዳም ወይን ጠጅ የተ​ጫኑ ሁለት አህ​ዮች እየ​ነዳ ተገ​ና​ኘው።


ሕዝ​ቡም ሁሉ እር​ሱን ተከ​ት​ለው ወጡ፤ ከበ​ሮ​ንና መሰ​ን​ቆ​ንም መቱ፥ በታ​ላ​ቅም ደስታ ደስ አላ​ቸው፤ ከጩ​ኸ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ምድር ተና​ወ​ጠች።


የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ደስ አላ​ቸው፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱም ፀጥ አለች። ጎቶ​ል​ያ​ንም በን​ጉሡ ቤት አጠ​ገብ በሰ​ይፍ ገደ​ሉ​አት።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ው​ላ​ቸው ነበ​ርና እየ​በ​ሉና እየ​ጠጡ በዚያ ከዳ​ዊት ጋር ሦስት ቀን ተቀ​መጡ።


ዳዊ​ትም ከሻ​ለ​ቆ​ችና ከመቶ አለ​ቆች፥ ከአ​ለ​ቆ​ቹም ሁሉ ጋር ተማ​ከረ።


በዚ​ያም ቀን በታ​ላቅ ደስታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሉ፥ ጠጡም። የዳ​ዊ​ት​ንም ልጅ ሰሎ​ሞ​ንን ሁለ​ተኛ ጊዜ አነ​ገ​ሡት፤ እር​ሱ​ንም ንጉሥ ይሆን ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀቡት፤ ሳዶ​ቅም በካ​ህ​ናት ላይ ተሾመ።


በጻድቃን ደግነት ከተማ ትቀናለች፥ በክፉዎችም ጥፋት ደስ ይላታል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ ሌሎች አማ​ል​ክት ቢመ​ለ​ሱና የዘ​ቢብ ጥፍ​ጥ​ፍን ቢወ​ድዱ እን​ኳን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ደ​ሚ​ወ​ድ​ዳ​ቸው አን​ተም ክፋ​ትና ዝሙት ያለ​ባ​ትን ሴት ውደድ” አለኝ።


አቤ​ግ​ያም ፈጥና፦ ሁለት መቶ እን​ጀራ፥ ሁለት አቁ​ማዳ የወ​ይን ጠጅ፥ አም​ስት የተ​ዘ​ጋጁ በጎች፥ አም​ስ​ትም መስ​ፈ​ሪያ በሶ፥ አንድ ጎሞር ዘቢብ፥ ሁለት መቶም የበ​ለስ ጥፍ​ጥፍ ወሰ​ደች፥ በአ​ህ​ዮ​ችም ላይ አስ​ጫ​ነች።


跟着我们:

广告


广告