Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 11:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ቁመ​ቱም አም​ስት ክንድ የነ​በ​ረ​ውን ረጅ​ሙን ግብ​ፃ​ዊ​ውን ሰው ገደለ፤ በግ​ብ​ፃ​ዊ​ውም እጅ የሸ​ማኔ መጠ​ቅ​ለያ የመ​ሰለ ጦር ነበረ፤ እርሱ ግን በትር ይዞ ወደ እርሱ ወረደ፥ ከግ​ብ​ፃ​ዊ​ውም እጅ ጦሩን ቀምቶ በገዛ ጦሩ ገደ​ለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ደግሞም ቁመቱ ዐምስት ክንድ የሆነ አንድ ግብጻዊ ገደለ፤ ግብጻዊው የሸማኔ መጠቅለያ የመሰለ ጦር በእጁ ቢይዝም፣ በናያስ ግን ቈመጥ ይዞ ገጠመው፤ ከግብጻዊው እጅ ጦሩን ነጥቆ በገዛ ጦሩ ገደለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ቁመቱም አምስት ክንድ የነበረውን ረጅሙን ግብጻዊውን ሰው ገደለ፤ በግብጻዊውም እጅ የሸማኔ መጠቅለያ የመሰለ ጦር ነበረ፤ እርሱ ግን በትር ይዞ ወደ እርሱ ወረደ፥ ከግብፃዊው እጅ ጦሩን ነጠቀው፥ በገዛ ጦሩም ገደለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 እንዲሁም በጣም ትልቅ ጦር ይዞ የነበረውን፥ ቁመቱ ከሁለት ሜትር በላይ የሆነውን፥ አንድ ግዙፍ ግብጻዊ ገድሎአል፤ ይኸውም በናያ በእጁ ከበትር በስተቀር ሌላ የጦር መሣሪያ ሳይዝ ወደ ግብጻዊው ቀርቦ ከመታው በኋላ ግብጻዊው ይዞት የነበረውን የሸማኔ መጠቅለያ የሚመስለውን የገዛ ጦሩን ቀምቶ ገደለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ቁመቱም አምስት ክንድ የነበረውን ረጅሙን ግብጻዊውን ሰው ገደለ፤ በግብጻዊውም እጅ የሸማኔ መጠቅለያ የመሰለ ጦር ነበረ፤ እርሱ ግን በትር ይዞ ወደ እርሱ ወረደ፤ ከግብጻዊው እጅ ጦሩን ነቅሎ በገዛ ጦሩ ገደለው።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 11:23
6 交叉引用  

የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ ያደ​ረ​ገው ይህ ነው፤ ስሙም በሦ​ስቱ ኀያ​ላን መካ​ከል የተ​ጠራ ነበረ።


ደግ​ሞም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ሰልፍ ነበረ፤ የያ​ዔ​ርም ልጅ ኤል​ያ​ናን የጌት ሰው የጎ​ል​ያ​ድን ወን​ድም ለሕ​ሜን ገደለ። የጦሩ የቦም እንደ ሸማኔ መጠ​ቅ​ለያ ሆኖ ተገኘ።


ከራ​ፋ​ይ​ንም ወገን የባ​ሳን ንጉሥ ዐግ ብቻ​ውን ቀርቶ ነበር፤ እነሆ፥ አል​ጋው የብ​ረት አልጋ ነበረ፤ እርሱ በአ​ሞን ልጆች ሀገር ዳርቻ አለ፤ ርዝ​መቱ ዘጠኝ ክንድ ወር​ዱም አራት ክንድ በሰው ክንድ ልክ ነበረ።


ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሰፈር የጌት ሰው ጎል​ያድ፥ ቁመ​ቱም ስድ​ስት ክንድ ከስ​ን​ዝር የሆነ፥ ኀይ​ለኛ ሰው መጣ።


ዳዊ​ትም ሮጦ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው ላይ ቆመ፤ ሰይ​ፉ​ንም ይዞ ከሰ​ገ​ባው መዘ​ዘው፤ ገደ​ለ​ውም፤ ራሱ​ንም ቈረ​ጠው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ዋና​ቸው እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ሸሹ።


የጦ​ሩም የቦ እንደ ሸማኔ መጠ​ቅ​ለያ ነበረ፤ የጦ​ሩም ሚዛን ስድ​ስት መቶ ሰቅል ብረት ነበረ፤ ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም በፊቱ ይሄድ ነበር።


跟着我们:

广告


广告