Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 11:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ለዳ​ዊ​ትም የነ​በ​ሩት ኀያ​ላን አለ​ቆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ስለ እስ​ራ​ኤል እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ያነ​ግ​ሡት ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ጋር በመ​ን​ግ​ሥቱ አጸ​ኑት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የዳዊት ኀያላን ሰዎች አለቆች እነዚህ ናቸው፤ እነርሱም እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት መንግሥቱ በምድሪቱ ሁሉ ትሰፋ ዘንድ ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋራ ሆነው ለመንግሥቱ ብርቱ ድጋፍ ሰጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ለዳዊትም የነበሩት የኃያላን አለቆች እነዚህ ናቸው፤ ስለ እስራኤል እንደ ተናገረው እንደ ጌታ ቃል ሊያነግሡት ከእስራኤል ሁሉ ጋር በመንግሥቱ ላይ አጸኑት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ዝነኞች የሆኑት የዳዊት ወታደሮች ስም ዝርዝር ከዚህ በታች እንደሚከተለው ነው፦ እነርሱም ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋር ሆነው እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ዳዊት እንዲነግሥ በጣም ረድተዋል። መንግሥቱም ጽኑና ኀያል እንዲሆን አድርገዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ለዳዊትም የነበሩት የኃያላን አለቆች እነዚህ ናቸው፤ ስለ እስራኤል እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ያነግሡት ዘንድ ከእስራኤል ሁሉ ጋር በመንግሥቱ ላይ አጸኑት።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 11:10
13 交叉引用  

አበ​ኔ​ርም ዳዊ​ትን፥ “ተነ​ሥቼ ልሂድ፤ ካንተ ጋርም ቃል ኪዳን እን​ዲ​ያ​ደ​ርጉ፥ ነፍ​ስ​ህም እንደ ወደ​ደች ሁሉን እን​ድ​ት​ገዛ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ለጌ​ታዬ ለን​ጉሥ ልሰ​ብ​ስብ” አለው። ዳዊ​ትም አበ​ኔ​ርን አሰ​ና​በ​ተው፤ በሰ​ላ​ምም ሄደ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ ወደ ኬብ​ሮን መጡ፤ ንጉሥ ዳዊ​ትም በኬ​ብ​ሮን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቃል ኪዳን ከእ​ነ​ርሱ ጋር አደ​ረገ፤ በሳ​ሙ​ኤ​ልም እጅ እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ ዳዊ​ትን ቀቡት።


ሁሉም ጽኑ​ዓን ኀያ​ላ​ንና በሠ​ራ​ዊቱ ላይ አለ​ቆች ነበ​ሩና በአ​ደጋ ጣዮች ላይ ዳዊ​ትን አገ​ዙት።


እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል የሳ​ኦ​ልን መን​ግ​ሥት ወደ እርሱ ይመ​ልሱ ዘንድ በኬ​ብ​ሮን ሳለ ወደ ዳዊት የመ​ጡት የሠ​ራ​ዊቱ አለ​ቆች ቍጥር ይህ ነው።


ጋሻና ጦር ተሸ​ክ​መው ለሰ​ልፍ የተ​ዘ​ጋጁ የይ​ሁዳ ልጆች ስድ​ስት ሺህ ስም​ንት መቶ ነበሩ።


እነ​ዚህ ሁሉ ዳዊ​ትን በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ ያነ​ግ​ሡት ዘንድ አር​በ​ኞ​ችና ሰል​ፈ​ኞች እየ​ሆኑ በፍ​ጹም ልባ​ቸው ወደ ኬብ​ሮን መጡ፤ ደግ​ሞም ከእ​ስ​ራ​ኤል የቀ​ሩት ሁሉ ዳዊ​ትን ያነ​ግ​ሡት ዘንድ አንድ ልብ ነበሩ።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ው​ላ​ቸው ነበ​ርና እየ​በ​ሉና እየ​ጠጡ በዚያ ከዳ​ዊት ጋር ሦስት ቀን ተቀ​መጡ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆ​ችና የሺህ አለ​ቆች፥ የመቶ አለ​ቆ​ችም ለን​ጉ​ሡና ለን​ጉሡ ትእ​ዛዝ ሁሉ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ሹማ​ምት እንደ ቍጥ​ራ​ቸው በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸው እነ​ዚህ ነበሩ። እነ​ዚ​ህም ክፍ​ሎች እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ሃያ አራት ሺህ ሆነው በዓ​መቱ ወራት ሁሉ በየ​ወሩ ይገ​ቡና ይወጡ ነበር።


ዳዊ​ትም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አለ​ቆች ሁሉና የፍ​ርድ አለ​ቆ​ችን፥ ንጉ​ሡ​ንም በየ​ተራ የሚ​ጠ​ብ​ቁ​ትን አለ​ቆ​ቹን፥ ሻለ​ቆ​ቹ​ንም፥ የመቶ አለ​ቆ​ቹ​ንም፥ በን​ጉ​ሡና በል​ጆቹ ሀብ​ትና ንብ​ረት ላይ፥ መባ ባለ​በት ላይ የተ​ሾ​ሙ​ትን ጃን​ደ​ረ​ቦ​ች​ንም፥ ኀያ​ላ​ኑ​ንና ሰል​ፈ​ኞ​ቹን ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሰበ​ሰበ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ እን​ዳ​ይ​ነ​ግሥ ለና​ቅ​ሁት ለሳ​ኦል የም​ታ​ለ​ቅ​ስ​ለት እስከ መቼ ነው? የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ሞል​ተህ ና፤ በል​ጆቹ መካ​ከል ለእኔ ንጉሥ አዘ​ጋ​ጅ​ቼ​አ​ለ​ሁና ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እል​ክ​ሃ​ለሁ” አለው።


跟着我们:

广告


广告