Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሶፎንያስ 1:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እናንተ በመክቴሽ ገበያ የምትኖሩ ዋይ በሉ፤ ነጋዴዎቻችሁ ሁሉ ይደመሰሳሉ፤ በብር የሚነግዱትም ሁሉ ይሞታሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እናንተ በመክቴሽ የምትኖሩ ሆይ አልቅሱ፥ የከነዓን ሕዝብ ሁሉ ይጠፋሉና፥ ብርም የሚመዝኑ ሁሉ ይቆረጣሉና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እናንተ ከከተማው በታችኛው ክፍል የምትኖሩ ሁሉ ነጋዴዎቻችሁ ስለሚወገዱና በብር የሚነግዱ ሁሉ ስለሚጠፉ ይህን ድምፅ በምትሰሙበት ጊዜ ‘ዋይ! ዋይ!’ እያላችሁ አልቅሱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እናንተ በመክቴሽ የምትኖሩ ሆይ፥ የከነዓን ሕዝብ ሁሉ ጠፍተዋልና፥ ብርም የተሸከሙ ሁሉ ተቈርጠዋልና አልቅሱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እናንተ በመክቴሽ የምትኖሩ ሆይ፥ የከነዓን ሕዝብ ሁሉ ጠፍተዋልና፥ ብርም የተሸከሙ ሁሉ ተቈርጠዋልና አልቅሱ።

参见章节 复制




ሶፎንያስ 1:11
16 交叉引用  

ብርን እንደ ዐፈር ቢከምር፣ ልብስንም እንደ ሸክላ ጭቃ ቢያከማች፣


እርሱ ያከማቸውን ጻድቃን ይለብሱታል፤ ብሩንም ንጹሓን ይከፋፈሉታል።


እናንተ እረኞች፤ አልቅሱ፤ ዋይ በሉ፤ እናንተ የመንጋው ጌቶች፤ በዐመድ ላይ ተንከባለሉ፤ የምትታረዱበት ቀን ደርሷልና፤ እንደ ውብ የሸክላ ዕቃ ወድቃችሁ ትከሰከሳላችሁ።


ስለዚህ ማቅ ልበሱ፤ ዕዘኑ፤ ዋይ በሉ፤ የእግዚአብሔር አስፈሪ ቍጣ፣ ከእኛ አልተመለሰምና።


የሰው ልጅ ሆይ፤ ይህ በሕዝቤ ላይ፣ በእስራኤልም መሳፍንት ሁሉ ላይ መጥቷልና፤ ጩኸት፣ ዋይታም አሰማ። እነርሱ ከሕዝቤ ጋራ በአንድ ላይ፣ ለሰይፍ ተጥለዋል፤ ስለዚህ ደረትህን ምታ።


ከጥፋት ቢያመልጡም እንኳ፣ ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፤ ሜምፎስም ትቀብራቸዋለች። የብር ሀብታቸውን ዳዋ ያለብሰዋል፤ ድንኳኖቻቸውንም እሾኽ ይወርሳቸዋል።


ካህናት ሆይ፤ ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ፤ እናንተ በመሠዊያው ፊት የምታገለግሉ፣ ዋይ በሉ፤ እናንተ በአምላኬ ፊት የምታገለግሉ፣ ኑ፤ ማቅ ለብሳችሁ ዕደሩ፤ የእህል ቍርባኑና የመጠጥ ቍርባኑ፣ ከአምላካችሁ ቤት ተቋርጧልና።


እናንተ ሰካራሞች፤ ተነሡ፤ አልቅሱ፤ እናንተ የወይን ጠጅ ጠጪዎች ሁሉ፤ ዋይ በሉ፤ ስለ አዲሱ የወይን ጠጅ ዋይ ብላችሁ አልቅሱ፤ አፋችሁ ላይ እንዳለ ተነጥቃችኋልና።


እናንተ በባሕር ዳርቻ የምትኖሩ፣ የከሊታውያን ሰዎች ሆይ፤ ወዮላችሁ! የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፤ በአንቺ ላይ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤ “ፍጹም አጠፋሻለሁ፤ ከነዋሪዎችሽም የሚተርፍ የለም።”


በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉ ምንቸቶች ሁሉ ለሰራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር የተቀደሱ ይሆናሉ፤ መሥዋዕት ለማቅረብ የሚመጡ ሁሉ ምንቸቶቹን በመውሰድ ያበስሉባቸዋል፤ በዚያ ቀን በእግዚአብሔር ጸባኦት ቤት ከእንግዲህ ወዲያ ከነዓናዊ አይገኝም።


ርግብ ሻጮችንም፣ “እነዚህን ከዚህ አስወጧቸው፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት!” አላቸው።


እንግዲህ እናንተ ሀብታሞች ስሙ፤ ስለሚደርስባችሁ መከራ አልቅሱ፤ ዋይ ዋይም በሉ።


跟着我们:

广告


广告