Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘካርያስ 12:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “የዳዊት ቤትና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ክብር ከይሁዳ ክብር እንዳይበልጥ እግዚአብሔር በመጀመሪያ የይሁዳን መኖሪያዎች ያድናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ጌታም፥ የዳዊትን ቤት ክብርና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ክብር፥ በይሁዳ ክብር ላይ እንዳይታበይ የይሁዳን ድንኳኖች በቅድሚያ ያድናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 “እኔ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ለይሁዳ ነገድ ድልን አጐናጽፋለሁ፤ ይህንንም የማደርገው የዳዊት ልጆች ክብርና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ክብር ከሌሎቹ የይሁዳ ነገድ ተወላጆች ከፍ ከፍ እንዳይል ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እግዚአብሔርም የዳዊት ቤት ክብርና የኢየሩሳሌም ሰዎች ክብር በይሁዳ ክብር ላይ እንዳይታበይ የይሁዳን ድንኳኖች አስቀድሞ ያድናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እግዚአብሔርም የዳዊት ቤት ክብርና የኢየሩሳሌም ሰዎች ክብር በይሁዳ ክብር ላይ እንዳይታበይ የይሁዳን ድንኳኖች አስቀድሞ ያድናል።

参见章节 复制




ዘካርያስ 12:7
20 交叉引用  

ነገር ግን ራሳችሁን በእኔ ላይ ከፍ ብታደርጉ፣ መዋረዴንም እኔን ለመሞገት ብትጠቀሙበት፣


በጭንቀቴ ደስ የሚላቸው፣ ይፈሩ፤ ግራም ይጋቡ፤ በእኔ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ፣ ዕፍረትንና ውርደትን ይከናነቡ።


እኔ፣ “ጠላቶቼ በእኔ ላይ ደስ አይበላቸው፤ እግሬም ሲንሸራተት፣ በላዬ አይኵራሩብኝ” ብያለሁና።


የሚዘልፈኝ ጠላት አይደለምና፤ ቢሆንማ ኖሮ በታገሥሁት ነበር፤ የሚጠላኝ፣ ራሱንም ቀና ቀና ያደረገብኝ ባላንጣ አይደለም፤ ቢሆንማ ከርሱ በተሸሸግሁ ነበር።


የክብርን ሁሉ ትዕቢት ሊያዋርድ፣ በምድር ከፍ ከፍ ያለውንም ሁሉ ዝቅ ሊያደርግ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወስኗል።


“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘እነሆ የያዕቆብን ድንኳን ምርኮ እመልሳለሁ፤ ለማደሪያውም እራራለሁ፤ ከተማዪቱ በፍርስራሿ ጕብታ ላይ ትሠራለች፤ ቤተ መንግሥቱም በቀድሞ ቦታው ይቆማል።


“በዚያ ቀን፣ “የወደቀውን የዳዊትን ድንኳን አነሣለሁ፤ የተሰበረውን እጠግናለሁ፤ ፍርስራሹን ዐድሳለሁ፤ ቀድሞ እንደ ነበረም አድርጌ እሠራዋለሁ፤


በዚያም ቀን ኪዳኑ ፈረሰ፤ ሲመለከቱኝ የነበሩትና የተጨነቁት በጎችም የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ዐወቁ።


ከዚያም እንዲህ አለኝ፤ “ለዘሩባቤል የተላከው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤ ‘በመንፈሴ እንጂ በኀይልና በብርታት አይደለም’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


በዚያ ጊዜ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሐሤት አድርጎ እንዲህ አለ፤ “የሰማይና የምድር ጌታ፤ አባት ሆይ፤ ይህን ከጥበበኞችና ከዐዋቂዎች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ፤ አዎን አባት ሆይ፤ ይህ የአንተ በጎ ፈቃድ ሆኗልና።


ታዲያ ትምክሕት ወዴት ነው? እርሱማ ቀርቷል። በየትኛው ሕግ? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፤ በእምነት ሕግ ነው እንጂ።


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለጠጋ እንዲሆኑና እርሱን ለሚወድዱም ተስፋ የተሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?


ነገር ግን ጸጋን አብዝቶ ይሰጠናል፤ መጽሐፍም፣ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” ያለው ስለዚህ ነው።


跟着我们:

广告


广告