Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 8:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 አንቺ በአትክልቱ ቦታ የምትኖሪ ሆይ፤ ባልንጀሮቼ ድምፅሽን ይሰማሉ፤ እስኪ እኔም ልስማው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በገነቱ የምትቀመጪ ሆይ፥ ባልንጀሮች የአንቺን ድምፅ ይሰማሉ፥ ድምፅሽን አሰሚኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 አንቺ የእኔ ሙሽራ ሆይ! በአትክልት ቦታ ሆነሽ ጓደኞቼ ድምፅሽን ለመስማት ይፈልጋሉ፤ እስቲ ለእኔ ድምፅሽን አሰሚኝ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በአ​ት​ክ​ልቱ ቦታ ሲኖር ሌሎች አዩት፥ ቃል​ህን አሰ​ማኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በገነቱ የምትቀመጪ ሆይ፥ ባልንጀሮች የአንቺን ቃል ያደምጣሉ፥ ቃልሽን አሰሚኝ።

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 8:13
19 交叉引用  

በጥልፍ ሥራ ባጌጠ ልብስ ወደ ንጉሥ ትወሰዳለች፤ ደናግል ጓደኞቿም ተከትለዋት፣ ወደ አንተ ይመጣሉ።


በመከራ ጊዜ ወደ እኔ ጩኽ፤ አድንሃለሁ፤ አንተም ታከብረኛለህ።”


ውዴ ሆይ፤ መንጋህን የት እንደምታሰማራ፣ በቀትርም የት እንደምትመስጋቸው እባክህ ንገረኝ፤ በወዳጆችህ መንጎች ኋላ፣ ፊቷን ሸፍና እንደምትቅበዘበዝ ሴት ለምን ልሁን?


የሰሜን ነፋስ ሆይ፤ ንቃ፤ የደቡብም ነፋስ ሆይ፤ ና! መዐዛው ያውድ ዘንድ፣ በአትክልት ቦታዬ ላይ ንፈስ፤ ውዴ ወደ አትክልት ቦታው ይግባ፤ ምርጥ ፍሬዎቹንም ይብላ።


በሸለቆው ውስጥ አዲስ የበቀሉትን አትክልቶች ለማየት፣ ወይኑ ማቈጥቈጡን፣ ሮማኑ ማበቡን ለመመልከት፣ ወደ ለውዙ ተክል ቦታ ወረድሁ።


ውዴ መንጋውን ለማሰማራት፣ ውብ አበቦችንም ለመሰብሰብ፣ የቅመማ ቅመም መደቦቹ ወዳሉበት፣ ወደ አትክልት ቦታው ወርዷል።


የወይኔ ተክል ቦታ የራሴ፣ የግሌ ነው፤ ሰሎሞን ሆይ፤ አንድ ሺሑ ሰቅል ለአንተ፤ ፍሬውን ለሚጠብቁ ደግም ሁለት መቶ ይሁን።


ሁለት ወይም ሦስት ሆነው በስሜ በሚሰበሰቡበት መካከል በዚያ እገኛለሁና።”


ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሯቸው፤ እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋራ ነኝ።”


በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ፣ የምትፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ለምኑ፤ ይሰጣችኋልም።


እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ለምኑ ትቀበላላችሁ፤ ደስታችሁም ሙሉ ይሆናል።


እርሱም፣ “በይ ሂጂ” ብሎ ለሁለት ወር አሰናበታት፤ እርሷም ከእንግዲህ ባል ስለማታገባ ከልጃገረድ ጓደኞቿ ጋራ ወደ ተራሮች ሄደው አለቀሱ።


እርሱም ለፍልስጥኤማውያን በታየ ጊዜ፣ ሠላሳ አጃቢዎች ሰጡት።


跟着我们:

广告


广告