Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 8:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ሰሎሞን በብኤላሞን የወይን ተክል ቦታ ነበረው፤ የወይኑን ተክል ቦታም ለአትክልተኞች አከራየው፤ እያንዳንዳቸውም የፍሬውን ዋጋ፣ አንድ አንድ ሺሕ ሰቅል ብር ያመጡለት ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ለሰሎሞን በብኤላሞን የወይን ቦታ ነበረው፥ የወይኑን ቦታ ለጠባቂዎች አከራየው፥ ሰው ሁሉ ለፍሬው ሺህ ብር ያመጣለት ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ሰሎሞን በባዓልሃሞን የወይን ተክል ቦታ ነበረው፤ የወይኑንም ተክል ቦታ ለአትክልተኞች አከራየው፤ እያንዳንዳቸውም አንድ ሺህ ብር ያመጡለት ነበር፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ለሰ​ሎ​ሞን በብ​ኤ​ላ​ሞን የወ​ይን ቦታ ነበ​ረው፤ የወ​ይ​ኑን ቦታ ፍሬ​ውን ለሚ​ጠ​ብቁ አከ​ራ​የው፤ ሰው ሁሉ በየ​ጊ​ዜው ለፍ​ሬው አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር ያመ​ጣል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ለሰሎሞን በብኤላሞን የወይን ቦታ ነበረው፥ የወይኑን ቦታ ለጠባቂዎች አከራየው፥ ሰው ሁሉ ለፍሬው ሺህ ብር ያመጣለት ነበር።

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 8:11
11 交叉引用  

ሣራንም፣ “እነሆ፤ ለወንድምሽ ለአብርሃም አንድ ሺሕ ጥሬ ብር እሰጠዋለሁ፤ ይህም በአንቺ ላይ ለተፈጸመው በደል ካሣ እንዲሆንና ዐብረውሽ ያሉ ሁሉ እንዲያውቁት ነው፤ በዚህም ንጽሕናሽ ይረጋገጣል” አላት።


ታላላቅ ነገሮችን አከናወንሁ፤ ለራሴ ቤቶችን ሠራሁ፤ ወይንንም ተከልሁ፤


ጥቍር ስለ ሆንሁ ትኵር ብላችሁ አትዩኝ፤ መልኬን ያጠቈረው ፀሓይ ነውና፤ የእናቴ ልጆች ወንድሞቼ ተቈጡኝ፤ የወይን ተክል ቦታዎችም ጠባቂ አደረጉኝ፤ የራሴን የወይን ተክል ቦታ ተውሁት።


በዱር ዛፎች መካከል እንዳለ እንኮይ፣ ውዴም በጕልማሶች መካከል እንዲሁ ነው፤ በጥላው ሥር መቀመጥ ደስ ያሰኛል፤ የፍሬውም ጣፋጭነት ያረካኛል።


ማልደን ወደ ወይኑ ተክል ቦታ እንሂድ፣ ወይኑ እንቡጥ አውጥቶ፣ አበባው ፈክቶ፣ ሮማኑ አፍርቶ እንደ ሆነ እንይ፤ በዚያም ራሴን በፍቅር እሰጥሃለሁ።


የወይኔ ተክል ቦታ የራሴ፣ የግሌ ነው፤ ሰሎሞን ሆይ፤ አንድ ሺሑ ሰቅል ለአንተ፤ ፍሬውን ለሚጠብቁ ደግም ሁለት መቶ ይሁን።


በዚያ ቀን ሺሕ ሰቅል ብር የሚያወጣ አንድ ሺሕ የወይን ተክል የነበረበት ቦታ ሁሉ፣ ኵርንችትና እሾኽ ብቻ ይሆናል።


ከዚያም እንዲህ እያለ በምሳሌ ይነግራቸው ጀመር፤ “አንድ ሰው ወይን ተከለ፤ ዙሪያውን ዐጠረ፤ ለመጭመቂያው ጕድጓድ ቈፈረ፤ የመጠበቂያም ማማ ሠራለት፤ ለገበሬዎችም አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።


跟着我们:

广告


广告