Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 7:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ትርንጐዎች መዐዛቸውን ሰጡ፤ አዲስ የተቀጠፈውም ሆነ የበሰለው፣ ጣፋጩ ፍሬ ሁሉ በደጃፋችን አለ፤ ውዴ ሆይ፤ ለአንተ አስቀምጬልሃለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ትርንጎዎች መዓዛን ሰጡ፥ መልካሞች ፍሬዎች ሁሉ፥ አሮጌው ከአዲሱ ጋር፥ በደጃችን አሉ፥ ውዴ ሆይ፥ ሁሉን ለአንተ ጠበቅሁልህ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 የእንኰይ ፍሬ መዓዛና እንዲሁም ደስ የሚያሰኙ ልዩ ልዩ ፍራፍሬዎች ደጃችንን ሞልተውታል። ውዴ ሆይ! ከነዚህም ፍሬዎች የበሰሉትንና አዲስ የተቀጠፉትን ለአንተ አኑሬልሃለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ወደ ወይኑ ቦታ ማልደን እንሂድ፤ ወይኑ አብቦ፥ አበባውም ፍሬ አንዠርግጎ ሮማኑም አፍርቶ እንደ ሆነ እንይ፤ በዚያ ጡቶቼን እሰጥሃለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ወደ ወይኑ ቦታ ማልደን እንሂድ፥ ወይኑ አብቦ አበባውም ፍሬ አንዠርግጎ ሮማኑም አፍርቶ እንደ ሆነ እንይ፥ በዚያ ውዴን እሰጥሃለሁ።

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 7:13
21 交叉引用  

ስንዴ በሚታጨድበት ወቅት፣ ሮቤል ወደ ሜዳ ወጣ፤ እንኮይም አግኝቶ ለእናቱ ለልያ አመጣላት። ራሔልም ልያን፣ “እባክሽን ልጅሽ ካመጣልሽ እንኮይ ስጪኝ” አለቻት።


በዱር ዛፎች መካከል እንዳለ እንኮይ፣ ውዴም በጕልማሶች መካከል እንዲሁ ነው፤ በጥላው ሥር መቀመጥ ደስ ያሰኛል፤ የፍሬውም ጣፋጭነት ያረካኛል።


ተክልሽ ሮማን፣ ምርጥ ፍሬዎች፣ ሄናና ናርዶስ ያሉበት ነው፤


የሰሜን ነፋስ ሆይ፤ ንቃ፤ የደቡብም ነፋስ ሆይ፤ ና! መዐዛው ያውድ ዘንድ፣ በአትክልት ቦታዬ ላይ ንፈስ፤ ውዴ ወደ አትክልት ቦታው ይግባ፤ ምርጥ ፍሬዎቹንም ይብላ።


በሸለቆው ውስጥ አዲስ የበቀሉትን አትክልቶች ለማየት፣ ወይኑ ማቈጥቈጡን፣ ሮማኑ ማበቡን ለመመልከት፣ ወደ ለውዙ ተክል ቦታ ወረድሁ።


ምነው አንተ የእናቴን ጡት እንደ ጠባ፣ እንደ ወንድሜ በሆንህ! ከዚያም ውጭ ባገኝህ፣ እስምህ ነበር፤ ታዲያ ማንም ባልናቀኝ!


ያም ሆኖ ትርፏና ያገኘችው ሁሉ ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናል፤ አይከማችም፤ አይጠራቀምም። ትርፏም በእግዚአብሔር ፊት ለሚኖሩት የተትረፈረፈ ምግብና ጥሩ ልብስ ይሆናል።


እርሱም፣ “ስለዚህም የመንግሥተ ሰማይን ምስጢር የተረዳ ማንኛውም የኦሪት ሕግ መምህር፣ ከከበረ ሀብቱ ክምችት አዲሱንም አሮጌውንም የሚያወጣ ባለንብረት ይመስላል” አላቸው።


“ንጉሡም መልሶ፣ ‘እውነት እላችኋለሁ፣ ከእነዚህ አነስተኛ ከሆኑት ወንድሞቼ ለአንዱ ያደረጋችሁት፣ ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው’ ይላቸዋል።


ብዙ ፍሬ በማፍራት ደቀ መዛሙርቴ መሆናችሁን ብትገልጡ፣ በዚህ አባቴ ይከብራል።


ገንዘብ ማሰባሰብ የሚደረገው እኔ በምመጣበት ጊዜ እንዳይሆን፣ ከእናንተ እያንዳንዱ እንደ ገቢው መጠን በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን እየለየ ያስቀምጥ።


ይሁን እንጂ እንደ ተጻፈው፣ “ዐይን ያላየውን፣ ጆሮ ያልሰማውን፣ የሰውም ልብ ያላሰበውን፣ እግዚአብሔር ለሚወድዱት አዘጋጅቷል፤”


የብርሃኑ ፍሬ በበጎነት፣ በጽድቅና በእውነት ሁሉ ዘንድ ነውና።


ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሚገኘው የጽድቅ ፍሬ እንድትሞሉ ነው።


በርሱ በኩል ለእግዚአብሔር አብ ምስጋና እያቀረባችሁ፣ በቃልም ሆነ በተግባር የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።


ከእናንተ ማንም የሚናገር ቢኖር እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢኖር እግዚአብሔር በሚሰጠው ብርታት ያገልግል፤ ይኸውም እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እንዲከብር ነው። ክብርና ኀይል ለርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን። አሜን።


跟着我们:

广告


广告