Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 5:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ፤ ውድሽ ከሌሎች እንዴት ቢበልጥ ነው? እስከዚህ የምትማጠኚንስ፣ ውድሽ ከሌሎች እንዴት ቢበልጥ ነው?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 አንቺ በሴቶች ዘንድ የተዋብሽ ሆይ፥ ከሌላ ወዳጅ ይልቅ ፍቅረኛሽ ምን አለው? ይህን የሚያህል የምታስምይን? ከሌላ ወዳጅ ይልቅ ፍቅረኛሽ ምን አለው?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ! በውኑ የአንቺ ፍቅረኛ ከሌሎች የተለየ ነውን? ስለ እርሱ ይህን ያኽል ዐደራ የምትዪን? እርሱ ከሌሎች የሚለይበት ነገር ምንድን ነው?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 አንቺ በሴ​ቶች ዘንድ የተ​ዋ​ብሽ ሆይ፥ ከወ​ን​ድ​ሞች ልጆች ይልቅ ልጅ ወን​ድ​ምሽ ማን ነው? ይህን ያህል መሐላ አም​ለ​ሽ​ና​ልና ከወ​ን​ድ​ሞች ልጆች ይልቅ ልጅ ወን​ድ​ምሽ ማን ነው?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 አንቺ በሴቶች ዘንድ የተዋብሽ ሆይ፥ ከሌላ ወዳጅ ይልቅ ውድሽ ማን ነው? ይህን የሚያህል አምለሽናልና ከሌላ ወዳጅ ይልቅ ውድሽ ማን ነው?

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 5:9
11 交叉引用  

የንጉሥ ልጅ ከላይ እስከ ታች ተሸልማ እልፍኟ ውስጥ አለች፤ ልብሷም ወርቀ ዘቦ ነው።


የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፤ ስለ አንቺ ክቡር የሆነ ነገር እንዲህ ተብሎ ይነገራል፤ ሴላ


አንቺ ከሴቶች ሁሉ ይበልጥ የተዋብሽ ሆይ፤ የማታውቂ ከሆነ፣ የበጎቹን ዱካ ተከተዪ፤ የፍየል ግልገሎችሽንም፣ በእረኞቹ ድንኳን አጠገብ አሰማሪ።


እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፣ ራሱ እስኪፈልግ ድረስ፣ ፍቅርን እንዳታስነሡት ወይም እንዳትቀሰቅሱት፣ በሚዳቋና በሜዳ ዋሊያ አማፅናችኋለሁ።


አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ፤ ውድሽ ወዴት ሄደ? ዐብረንሽም እንድንፈልገው፣ ውድሽ የሄደው በየት በኩል ነው?


በፊቱ እንደ ቡቃያ፣ ከደረቅም መሬት እንደ ወጣ ሥር በቀለ፤ የሚስብ ውበት ወይም ግርማ የለውም፤ እንድንወድደውም የሚያደርግ መልክ አልነበረውም።


ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜም ከተማዋ በመላ፣ “ይህ ማነው?” በማለት ታወከች።


ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በመካከላችንም ዐደረ፤ እኛም ጸጋንና እውነትን ተሞልቶ ከአባቱ ዘንድ የመጣውን የአንድያ ልጅን ክብር አየን።


跟着我们:

广告


广告