Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 5:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ለውዴ ልከፍትለት ተነሣሁ፤ በከርቤ ነጠብጣብ የራሱት እጆቼ፣ በከርቤም ፈሳሽ የተነከሩት ጣቶቼ፣ የመወርወሪያውን እጀታ ያዙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ለውዴ እከፍትለት ዘንድ ተነሣሁ፥ እጆቼ በደጁ መወርወሪያ ላይ ከርቤን አፈሰሱ፥ ጣቶቼ ፈሳሹን ከርቤ አንጠባጠቡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ስለዚህ ለውዴ በሩን ልከፍትለት ተነሣሁ፤ የበሩን መክፈቻ እጀታ ስይዘው እጆቼ ከርቤ አንጠባጠቡ፤ ጣቶቼም የከርቤ ፈሳሽ አፈሰሱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ለልጅ ወን​ድሜ እከ​ፍ​ት​ለት ዘንድ ተነ​ሣሁ፤ እጆች በደጁ መወ​ር​ወ​ሪያ ላይ ከር​ቤን አፈ​ሰሱ፥ ጣቶች ፈሳ​ሹን ከርቤ አን​ጠ​ባ​ጠቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ለውዴ እከፍትለት ዘንድ ተነሣሁ፥ እጆቼ በደጁ መወርወሪያ ላይ ከርቤን አፈሰሱ፥ ጣቶቼ ፈሳሹን ከርቤ አንጠበጠቡ።

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 5:5
10 交叉引用  

አንተ ውዴ ሆይ፤ እንዴት ውብ ነህ! እንዴትስ ታምራለህ! ዐልጋችንም እንደ ለምለም ሣር ነው።


ከከርቤና ከዕጣን፣ ከነጋዴም ቅመማ ቅመም ሁሉ በተዘጋጀ ሽቱ፣ መዐዛዋ የሚያውድ፣ እንደ ጢስ ዐምድ ከምድረ በዳ የምትወጣው ይህች ማን ናት?


ጕንጮቹ የሽቱ መዐዛ የሚያመጡ፣ የቅመማ ቅመም መደቦችን ይመስላሉ፤ ከንፈሮቹም ከርቤ እንደሚያንጠባጥቡ፣ ውብ አበቦች ናቸው።


እኔ ተኝቻለሁ፤ ልቤ ግን ነቅቷል፤ ስሙ! ውዴ በር ያንኳኳል፤ እንዲህ ይላል፤ “እኅቴ ወዳጄ፣ ርግቤ፣ አንቺ እንከን የሌለብሽ፤ ክፈቺልኝ። ራሴ በጤዛ፣ ጠጕሬም በሌሊቱ ርጥበት ረስርሷል።”


ጌታቸው ከሰርግ ግብዣ እስኪመለስ የሚጠባበቁና መጥቶም በር ሲያንኳኳ ወዲያው ለመክፈት ዝግጁ የሆኑ ሰዎችን ምሰሉ።


የተጽናናነውም በመምጣቱ ብቻ ሳይሆን፣ እርሱንም ልታጽናኑት በመቻላችሁ ጭምር ነው። ስለ ናፍቆታችሁ፣ ስለ ሐዘናችሁና ለእኔም ስላላችሁ ቅናት ነግሮናል፤ ስለዚህ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ደስ ብሎኛል።


ይኸውም በእምነት ክርስቶስ በልባችሁ እንዲያድር ነው። ደግሞም ሥር ሰድዳችሁ፣ በፍቅር ታንጻችሁ፣


እነሆ፤ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ሰምቶ በሩን ቢከፍትልኝ ወደ እርሱ ገብቼ ከርሱ ጋራ እበላለሁ፤ እርሱም ከእኔ ጋራ ይበላል።


跟着我们:

广告


广告