Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 3:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ተነሥቼ ወደ ከተማዪቱ እወጣለሁ፤ በዋና ዋና መንገዶችና በአደባባዮች እዘዋወራለሁ፤ ውዴንም እፈልገዋለሁ፤ ስለዚህም ፈለግሁት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እነሣለሁ በከተማይቱም እዞራለሁ፥ ነፍሴ የወደደችውን በጎዳናና በአደባባይ እፈልጋለሁ፥ ፈለግሁት አላገኘሁትም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 አሁን ተነሥቼ በከተማው አካባቢ በመንገዶችና በአደባባዮች መካከል ልቤ የምትወደውን እፈልገዋለሁ፤ ፈለግኹት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እነ​ሣ​ለሁ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም እዞ​ራ​ለሁ፥ ነፍሴ የወ​ደ​ደ​ች​ውን በገ​በ​ያና በአ​ደ​ባ​ባይ እፈ​ል​ጋ​ለሁ፤ ፈለ​ግ​ሁት አላ​ገ​ኘ​ሁ​ትም። ጠራ​ሁት አል​መ​ለ​ሰ​ል​ኝም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እነሣለሁ በከተማይቱም እዞራለሁ፥ ነፍሴ የወደደችውን በጎዳናና በአደባባይ እፈልጋለሁ፥ ፈለግሁት አላገኘሁትም።

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 3:2
18 交叉引用  

ብፁዕ ነው፤ በየዕለቱ ደጃፌ ላይ የሚጠብቅ፣ በበራፌ ላይ የሚጠባበቅ፣ የሚያዳምጠኝ ሰው፤


ውዴ ሆይ፤ መንጋህን የት እንደምታሰማራ፣ በቀትርም የት እንደምትመስጋቸው እባክህ ንገረኝ፤ በወዳጆችህ መንጎች ኋላ፣ ፊቷን ሸፍና እንደምትቅበዘበዝ ሴት ለምን ልሁን?


በከተማዪቱ ውስጥ ሲዘዋወሩ፣ የከተማዪቱ ጠባቂዎች አገኙኝ፤ እኔም፣ “ውዴን አይታችኋል?” አልኋቸው።


ለውዴ ልከፍትለት ተነሣሁ፤ በከርቤ ነጠብጣብ የራሱት እጆቼ፣ በከርቤም ፈሳሽ የተነከሩት ጣቶቼ፣ የመወርወሪያውን እጀታ ያዙ።


ማንም በጸሎት ስምህን አይጠራም፤ አንተንም ለመያዝ የሚሞክር የለም፤ ፊትህን ከእኛ ሰውረሃል፤ ስለ ኀጢአታችንም ትተኸናል።


“በኢየሩሳሌም መንገዶች እስኪ ውጡ፤ ወደ ላይ ወደ ታችም ውረዱ፤ ዙሪያውን ተመልከቱ ቃኙ፤ በአደባባይዋም ፈልጉ፤ እውነትን የሚሻና በቅንነት የሚሄድ፣ አንድ ሰው እንኳ ብታገኙ፣ እኔ ይህችን ከተማ እምራታለሁ።


ከእግዚአብሔር የተላከ ዮሐንስ የተባለ አንድ ሰው ነበረ።


ዘመኑን በማስተዋል ይህን አድርጉ፤ ከእንቅልፋችሁ የምትነቁበት ጊዜ አሁን ነው፤ መዳናችን መጀመሪያ ካመንበት ጊዜ ይልቅ አሁን ወደ እኛ ቀርቧልና።


ወደ ሰከነ ልቡናችሁ ተመለሱ፤ ኀጢአትንም አትሥሩ፤ እግዚአብሔርን የማያውቁ አሉና፤ ይህንም የምለው ላሳፍራችሁ ነው።


ምክንያቱም ሁሉን ነገር እንዲታይ የሚያደርገው ብርሃን ነውና፤ ስለዚህም፣ “አንተ የተኛህ ንቃ፤ ከሙታን ተነሣ፤ ክርስቶስም ያበራልሃል” ተብሏል።


跟着我们:

广告


广告