Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማሕልየ መሓልይ 2:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ውዴ ሚዳቋ ወይም የዋሊያ ግልገል ይመስላል፤ እነሆ፤ ከቤታችን ግድግዳ ኋላ ቆሟል፤ በመስኮት ትክ ብሎ ወደ ውስጥ ያያል፤ በፍርግርጉም እያሾለከ ይመለከታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ውዴ ሚዳቋን ወይም የዋላን እምቦሳ ይመስላል፥ እነሆ፥ በመስኮቶች ሲጐበኝ፥ በዓይነ ርግብም ሲመለከት፥ እርሱ ከቅጥራችን በኋላ ቆሞአል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ውዴ፥ ዋልያ ወይም የአጋዘን ግልገል ይመስላል፤ እነሆም ከቤታችን ቅጽር አጠገብ ቆሞአል፤ በመስኮትም ወደ ውስጥ ይመለከታል፤ በዐይነ ርግቡ ቀዳዳ በኩል አሾልኮ ይቃኛል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ልጅ ወን​ድሜ በቤ​ቴል ተራ​ሮች ላይ ሚዳ​ቋን ወይም የዋ​ሊ​ያን እን​ም​ቦሳ ይመ​ስ​ላል፤ እነሆ፥ በመ​ስ​ኮ​ቶች ሲጐ​በኝ፥ በዐ​ይነ ርግ​ብም ሲመ​ለ​ከት፥ እርሱ ከቅ​ጥ​ራ​ችን በኋላ ቆሞ​አል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ውዴ ሚዳቋን ወይም የዋላን እምቦሳ ይመስላል፥ እነሆ፥ በመስኮቶች ሲጐበኝ፥ በዓይነ ርግብም ሲመለከት፥ እርሱ ከቅጥራችን በኋላ ቆሞአል።

参见章节 复制




ማሕልየ መሓልይ 2:9
23 交叉引用  

ሦስቱ የጽሩያ ወንዶች ልጆች ኢዮአብ፣ አቢሳና አሣሄል እዚያው ነበሩ። አሣሄል እንደ ዱር ሚዳቋ በሩጫ ፈጣን ነበረ።


እርሷ እንደ ተወደደች ዋላ፣ እንደ ተዋበች ሚዳቋ ናት፤ ጡቶቿ ዘወትር ያርኩህ፤ ፍቅሯም ሁልጊዜ ይማርክህ።


ከዐዳኝ እጅ እንዳመለጠች ሚዳቋ፣ ከአጥማጅ ወጥመድ እንዳፈተለከች ወፍ ራስህን አድን።


በቤቴ መስኮት፣ በዐይነ ርግቡ ወደ ውጭ ተመለከትሁ።


አንተ ውዴ ሆይ፤ እንዴት ውብ ነህ! እንዴትስ ታምራለህ! ዐልጋችንም እንደ ለምለም ሣር ነው።


ጎሕ ከመቅደዱ በፊት፣ ጥላውም ሳይሸሽ፣ ውዴ ሆይ፤ ተመለስ፤ ሚዳቋን ምሰል፤ ወይም በወጣ ገባ ኰረብቶች እንዳለው የዋሊያ ግልገል ሁን።


እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፣ ራሱ እስኪፈልግ ድረስ፣ ፍቅርን እንዳታስነሡት ወይም እንዳትቀሰቅሱት፣ በሚዳቋና በሜዳ ዋሊያ አማፅናችኋለሁ።


እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፤ ራሱ እስኪፈልግ ድረስ፣ ፍቅርን እንዳታስነሡት ወይም እንዳትቀሰቅሱት፣ በሚዳቋና በሜዳ ዋሊያ አማፅናችኋለሁ።


ውዴ ሆይ፤ ቶሎ ናልኝ፤ ሚዳቋን፣ ወይም በቅመም ተራራ ላይ የሚዘልል፣ የዋሊያን ግልገል ምሰል።


ሁለቱ ደቀ መዛሙርትም በመንገድ ላይ የሆነውንና ኢየሱስ እንጀራውን በቈረሰ ጊዜ እንዴት እንዳወቁት ተረኩላቸው።


ኢሳይያስ ይህን ያለው የኢየሱስን ክብር ስላየ ነው፤ ስለ እርሱም ተናገረ።


በእነርሱ የዘላለም ሕይወትን የምታገኙ እየመሰላችሁ፣ መጻሕፍትን ትመረምራላችሁ፤ እነዚሁ መጻሕፍት ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤


ሙሴን ብታምኑ ኖሮ፣ እኔን ባመናችሁ ነበር፤ ምክንያቱም እርሱ የጻፈው ስለ እኔ ነው።


አሁን የምናየው በመስተዋት ውስጥ እንደሚታይ በድንግዝግዝ ነው፤ በዚያ ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን። አሁን የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያ ጊዜ እኔ ራሴ ሙሉ በሙሉ የታወቅሁትን ያህል ዐውቃለሁ።


እነዚህ ሊመጡ ላሉ ነገሮች ጥላ ናቸውና፤ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው።


ሕጉ ወደ ፊት ለሚመጡት መልካም ነገሮች ጥላ ነው እንጂ እውነተኛው አካል አይደለም፤ ስለዚህም በየዓመቱ ዘወትር ያለ ማቋረጥ የሚቀርበው ተደጋጋሚ መሥዋዕት፣ ለአምልኮ የሚቀርቡትን ሰዎች ፍጹም ሊያደርጋቸው ከቶ አይችልም።


እኔም ልሰግድለት በእግሩ ሥር ተደፋሁ፤ እርሱ ግን፣ “ተው! ይህን አታድርግ! እኔም ከአንተና የኢየሱስን ምስክር ከያዙት ወንድሞችህ ጋራ አገልጋይ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና” አለኝ።


“የሲሣራ እናት በመስኮት ተመለከተች፤ በዐይነ ርግቡ ቀዳዳም ጮኻ ተጣራች፤ ‘ለምን ሠረገላው ሳይመጣ ዘገየ? የሠረገሎቹስ ድምፅ ለምን ጠፋ?’ አለች።


跟着我们:

广告


广告