ማሕልየ መሓልይ 1:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ውዴ ሆይ፤ መንጋህን የት እንደምታሰማራ፣ በቀትርም የት እንደምትመስጋቸው እባክህ ንገረኝ፤ በወዳጆችህ መንጎች ኋላ፣ ፊቷን ሸፍና እንደምትቅበዘበዝ ሴት ለምን ልሁን? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ነፍሴ የወደደችህ አንተ ንገረኝ፥ ወዴት ታሰማራለህ? በቀትርስ ጊዜ ወዴት ትመስጋለህ? ስለ ምንስ ከባልንጀሮችህ መንጎች በኋላ እቅበዘበዛለሁ? 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ውዴ ሆይ! እስቲ ንገረኝ፤ የበጎችህን መንጋ የምታሰማራው የት ነው? በቀትርስ ጊዜ ዕረፍት ያገኙ ዘንድ እንዲመሰጉ የምታደርገው የት ነው? አንተን በመፈለግ የጓደኞችህን መንጋ በመከተል ፊትዋን እንደ ሸፈነች ሴት የምቅበዘበዘው ለምንድን ነው? 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ነፍሴ የወደደችህ አንተ ንገረኝ፤ በባልንጀሮችህ መንጎች መካከል የተቅበዘበዝሁ እንዳልሆን፥ ወዴት ታሰማራለህ? በቀትርስ ጊዜ ወዴት ትመሰጋለህ? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ነፍሴ የወደደችህ አንተ ንገረኝ፥ ወዴት ታሰማራለህ? በቀትርስ ጊዜ ወዴት ትመስጋለህ? ስለ ምንስ ከባልንጀሮችህ መንጎች በኋላ እቅበዘበዛለሁ? 参见章节 |