Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሩት 1:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ኑኃሚን ግን እንዲህ አለቻቸው፤ “ልጆቼ ሆይ፤ ወደየቤታችሁ ተመለሱ፤ ከእኔ ጋራ ለምን ትሄዳላችሁ? ባል የሚሆኗችሁ ሌሎች ልጆች ከእንግዲህ የምወልድ ይመስላችኋልን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ናዖሚም አለች፦ “ልጆቼ ሆይ፥ ተመለሱ፥ ለምን ከእኔ ጋር ትሄዳላችሁ? ለእናንተ ባሎች የሚሆኑ ልጆች በማህፀኔ ይዣለሁን?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ናዖሚም እንዲህ አለቻቸው፤ “ልጆቼ ሆይ! እባካችሁ ተመለሱ፤ ከእኔ ጋር ለመሄድ የምትፈልጉት ለምንድነው? ለእናንተ ባሎች የሚሆኑ ልጆች እንደገና መውለድ የምችል ይመስላችኋልን?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ኑኃሚንም አለች፦ ልጆቼ ሆይ፥ ተመለሱ፣ ለምን ከእኔ ጋር ትሄዳላችሁ? ባሎቻችሁ የሚሆኑ ልጆች በሆዴ አሉኝን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ኑኃሚንም አለች “ልጆቼ ሆይ! ተመለሱ፤ ለምን ከእኔ ጋር ትሄዳላችሁ? ባሎቻችሁ የሚሆኑ ልጆች በሆዴ አሉኝን?

参见章节 复制




ሩት 1:11
5 交叉引用  

ከዚያም ይሁዳ ምራቱን ትዕማርን፣ “ልጄ ሴሎም ለአካለ መጠን እስኪደርስ ድረስ ወደ አባትሽ ቤት ሄደሽ መበለት ሆነሽ ብትኖሪ ይሻላል” አላት። ይህን ያለውም፣ ሴሎም እንደ ወንድሞቹ ተቀሥፎ ይሞትብኛል ብሎ ስለ ሠጋ ነበር። ትዕማርም እንዳላት ሄደች፤ በአባቷም ቤት ተቀመጠች።


አውናን ግን የሚወለደው ልጅ የርሱን ስም የሚያስጠራ እንደማይሆን ስላወቀ፣ ከወንድሙ ሚስት ጋራ ሩካቤ ሥጋ በፈጸመ ቍጥር የወንድሙንም ስም የሚያስጠራ ልጅ እንዳይወልድ ዘሩን በምድር ላይ ያፈስስ ነበር።


ወንድማማቾች በአንድነት ቢኖሩና ከእነርሱ አንዱ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት፣ የሟቹ ሚስት ከቤተ ሰቡ ውጭ ባል ማግባት የለባትም። የባሏ ወንድም ይውሰዳትና ያግባት፤ የዋርሳነት ግዴታውንም ይፈጽምላት።


ቀጥለውም፣ “አይሆንም! ከአንቺ ጋራ ተመልሰን ወደ ወገኖችሽ እንሄዳለን” አሏት።


ወደየቤታችሁ ተመለሱ፣ ልጆቼ፤ ሌላ ባል እንዳላገባ እጅግ አርጅቻለሁ፤ አሁንም ተስፋ አለኝ ብል፣ ዛሬ ማታ አግብቼ ከዚያም ልጆች ብወልድ፣


跟着我们:

广告


广告