ሮሜ 3:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም7 “የእኔ ውሸተኛ መሆን የእግዚአብሔርን እውነተኛነት የሚያጐላ፣ ክብሩንም የሚጨምርለት ከሆነ፣ ኀጢአተኛ ተብዬ እስካሁን እንዴት ይፈረድብኛል?” በማለት ሊከራከር የሚችል ሰው ይኖር ይሆናል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ነገር ግን የእግዚአብሔር እውነተኛነት በእኔ ውሸት ለክብሩ ከሞላ፥ ለምን እኔ እስካሁን እንደ ኃጢአተኛ ይፈረድብኛል? 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ነገር ግን የእኔ ሐሰተኛነት የእግዚአብሔርን እውነት በመግለጥ፥ የክብሩን ብዛት የሚያሳይ ከሆነ ታዲያ፥ እኔ እንደ ኃጢአተኛ የሚፈረድብኝ ስለ ምንድን ነው? 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 የእግዚአብሔር እውነት በእኔ ሐሰተናነት ለክብሩ ከፍ ከአለ እንግዲህ እኔን እንደ ኀጢአተና ለምን ይፈርድብናል? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 በእኔ ውሸት ግን የእግዚአብሔር እውነት ለክብሩ ከላቀ ስለምን በእኔ ደግሞ እንደ ኃጢአተኛ ገና ይፈርድብኛል? 参见章节 |