ሮሜ 15:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም24 ይህን ዕቅድ ወደ እስጳንያ በምሄድበት ጊዜ ልፈጽመው ዐስባለሁ። በማልፍበትም ጊዜ ልጐበኛችሁና ከእናንተ ጋራ ለጥቂት ጊዜ ቈይቼ ናፍቆቴን ከተወጣሁ በኋላ በጕዞዬ እንደምትረዱኝ ተስፋ አደርጋለሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 ወደ ስፔን በምሄድበት ጊዜ፥ ከእናንተ ጋር ተደስቼ ጥቂት ካሳላፍሁ በኋላ በጉዞዬ እንድትረዱኝ ሳልፍ ላያችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 ወደ እስፔን በምሄድበት ጊዜ እግረ መንገዴን ልጐበኛችሁ ዐቅጃለሁ። ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ደስ ብሎኝ ከቈየሁ በኋላ ጒዞዬን ለመቀጠል የሚያስችለኝን ርዳታ እንደምታደርጉልኝ ተስፋ አደርጋለሁ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 ወደ አስባንያ ስሄድ እግረ መንገዴን ላያችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ቀደም ብዬ ከእናንተ ጋር ደስ ካለኝ በኋላም ከእናንተ ወደዚያ እሄዳለሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 ወደ እስጳንያ በሄድሁ ጊዜ ሳልፍ እናንተን እንዳይ፥ አስቀድሜም ጥቂት ብጠግባችሁ ወደዚያ በጉዞዬ እንድትረዱኝ ተስፋ አደርጋለሁ። 参见章节 |