Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ራእይ 9:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እንደ ጊንጥም ያለ፣ ጅራትና መንደፊያ ነበራቸው፤ ደግሞም ሰዎችን ዐምስት ወር የሚያሠቃዩበት ኀይል በጅራታቸው ላይ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እንደ ጊንጥም ጅራት ያለ ጅራት አላቸው፤ በጅራታቸውም መውጊያ አለ፤ ሰዎችንም ለአምስት ወር ያህል የመጉዳት ሥልጣን አላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እንደ ጊንጥ ጅራትና መንደፊያ ነበራቸው፤ በጅራታቸው ውስጥ ሰዎችን ለአምስት ወር የሚጐዱበት ኀይል ነበራቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እንደ ጊንጥም ጅራት ያለ ጅራት አላቸው፤ በጅራታቸውም መውጊያ አለ፤ ሰዎችንም አምስት ወር እንዲጐዱ ሥልጣን አላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እንደ ጊንጥም ጅራት ያለ ጅራት አላቸው በጅራታቸውም መውጊያ አለ፥ ሰዎችንም አምስት ወር እንዲጐዱ ሥልጣን አላቸው።

参见章节 复制




ራእይ 9:10
7 交叉引用  

አባቴ ከባድ ቀንበር ጫነባችሁ፤ እኔ ግን የባሰ አከብደዋለሁ፤ አባቴ በዐለንጋ ገረፋችሁ፤ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ።’ ”


እርሱም ወጣቶቹ በሰጡት ምክር መሠረት፣ “አባቴ ቀንበራችሁን አከበደባችሁ፤ እኔ ደግሞ የባሰ አከብደዋለሁ፤ አባቴ በዐለንጋ ገረፋችሁ፤ እኔ ደግሞ በጊንጥ እገርፋችኋለሁ” አላቸው።


አንተ የሰው ልጅ ሆይ፤ እነርሱን ወይም ቃላቸውን አትፍራ፤ ኵርንችትና እሾኽ በዙሪያህ ቢኖሩም፣ በጊንጦች መካከል ብትቀመጥም አትፍራ። እነርሱ ዐመፀኛ ቤት ቢሆኑም፣ አንተ በሚሉህ ነገር አትፍራ፤ እነርሱም አያስደንግጡህ።


ወይስ ዕንቍላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋልን?


የፈረሶቹ ኀይል በአፋቸውና በጅራታቸው ላይ ነበር፤ ጅራታቸውም እባብ ይመስል ነበር፤ ራስ ስላላቸው ጕዳት የሚያደርሱት በርሱ ነበር።


ከጢሱም አንበጦች ወጥተው በምድር ላይ ወረዱ፤ እንደ ምድር ጊንጦች ሥልጣን ያለ ሥልጣን ተሰጣቸው።


እነርሱንም ዐምስት ወር ብቻ እንዲያሠቃዩአቸው እንጂ እንዲገድሏቸው ሥልጣን አልተሰጣቸውም፤ የሚሠቃዩትም ሥቃይ ጊንጥ ሰውን ሲነድፍ እንደሚሰማው ዐይነት ሥቃይ ነው።


跟着我们:

广告


广告