Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ራእይ 18:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ስለዚህ መቅሠፍቶቿ በአንድ ቀን ይመጡባታል፤ ሞት፣ ሐዘንና ራብ ይሆኑባታል፤ የሚፈርድባት ጌታ እግዚአብሔር ብርቱ ስለ ሆነ፣ በእሳት ትቃጠላለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ስለዚህም ሞትና ኀዘን፥ ራብም የሆኑት መቅሰፍቶችዋ በአንድ ቀን ይመጣሉ፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት ጌታ እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ስለዚህ መቅሠፍቶችዋ ሁሉ በአንድ ቀን ይደርሱባታል፤ ሞትና ሐዘን ራብም ይደርሱባታል፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ በእርስዋ ላይ የሚፈርድባት ጌታ አምላክ ብርቱ ነው።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ስለዚህ በአንድ ቀን ሞትና ሐዘን ራብም የሆኑ መቅሰፍቶችዋ ይመጣሉ፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ስለዚህ በአንድ ቀን ሞትና ኀዘን ራብም የሆኑ መቅሰፍቶችዋ ይመጣሉ፥ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።

参见章节 复制




ራእይ 18:8
18 交叉引用  

የኀይል ነገር ከተነሣ፣ እርሱ ኀያል ነው! የፍትሕም ነገር ከተነሣ፣ መጥሪያ ሊሰጠው የሚችል ማን ነው?


እግዚአብሔር አንድ ነገር ተናገረ፤ እኔም ይህን ሁለት ጊዜ ሰማሁ፤ ኀይል የእግዚአብሔር ነው።


በዚያ ቀን እግዚአብሔር፣ ተወርዋሪውን እባብ ሌዋታንን፣ የሚጠቀለለውን ዘንዶ ሌዋታንን በብርቱ፣ በታላቁና በኀይለኛ ሰይፍ ይቀጣዋል፤ የባሕሩንም ግዙፍ አውሬ ይቈራርጠዋል።


ስለዚህ እግዚአብሔር ራስንና ጅራትን፣ የዘንባባውን ቅርንጫፍና ሸንበቆውን ከእስራኤል በአንድ ቀን ይቈርጣል።


“አንተ ትዕቢተኛ፤ እነሆ፤ በአንተ ላይ ተነሥቻለሁ፤” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ “የምትቀጣበት ጊዜ፣ ቀንህ ደርሷልና።


ነገር ግን ቤዛቸው ብርቱ ነው፤ ስሙም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ ለምድራቸው ዕረፍትን ለመስጠት፤ ተግቶ ይሟገትላቸዋል፤ በባቢሎን የሚኖሩትን ግን ዕረፍት ይነሣቸዋል።


የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ወፍራሙ የባቢሎን ቅጥር ፈጽሞ ይፈርሳል፤ ከፍ ያሉት ደጆቿም በእሳት ይቃጠላሉ፤ ሰዎቹ በከንቱ ይደክማሉ፤ የሕዝቡም ልፋት ለእሳት ይሆናል።”


“ከባቢሎን ሸሽታችሁ ውጡ! ፈጥናችሁም ሕይወታችሁን አትርፉ! በኀጢአቷ ምክንያት አትጥፉ። የእግዚአብሔር የበቀል ጊዜ ነው፤ እርሱም የሥራዋን ይከፍላታል።


በሰራዊቱ ፊት፣ እግዚአብሔር ያንጐደጕዳል፤ የሰራዊቱ ብዛት ስፍር ቍጥር የለውም፤ ትእዛዙንም የሚያደርግ እርሱ ኀያል ነው፤ የእግዚአብሔር ቀን ታላቅ፣ እጅግም የሚያስፈራ ነው፤ ማንስ ሊቋቋመው ይችላል?


ጌታን እናስቀናውን? በብርታትስ ከርሱ እንበልጣለንን?


እንዲህም አሉ፤ “ያለህና የነበርህ፣ ሁሉን ቻይ፣ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ እናመሰግንሃለን፤ ምክንያቱም አንተ ታላቁን ኀይልህን ይዘህ ነግሠሃል።


አውሬውና ያየሃቸው ዐሥሩ ቀንዶች አመንዝራዪቱን ይጠሏታል፤ ባዶዋንና ዕራቍቷን ያስቀሯታል። ሥጋዋን ይበላሉ፤ በእሳትም ያቃጥሏታል።


ያየሃትም ሴት በምድር ነገሥታት ላይ የምትነግሥ ታላቂቱ ከተማ ናት።”


ያ ሁሉ ሀብት በአንድ ሰዓት ውስጥ ጠፋ።’ “የመርከብ አዛዦች ሁሉ፣ በመርከብ የሚጓዙ መንገደኞች ሁሉ፣ የመርከብ ሠራተኞችና ኑሯቸውን በባሕር ላይ የመሠረቱ ሁሉ በሩቅ ይቆማሉ።


በራሳቸውም ላይ አቧራ ነስንሰው እያለቀሱና እያዘኑ እንዲህ ብለው ጮኹ፤ “ ‘በባሕር ላይ መርከቦች ያላቸው ሁሉ፣ በርሷም ሀብት የበለጸጉ፣ ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት! ወዮላት! በአንድ ሰዓት ውስጥ ጠፍታለች!’


ደግሞም እንዲህ አሉ፤ “ሃሌ ሉያ! ጢስ ከርሷ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይወጣል።”


跟着我们:

广告


广告