Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ራእይ 18:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 የበገና ደርዳሪዎችና የሙዚቀኞች ድምፅ፣ የዋሽንትና የመለከት ነፊዎች ድምፅ፣ ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ አይሰማም፤ የእጅ ጥበብ ባለሙያ፣ ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ አይገኝም፤ የወፍጮ ድምፅም፣ ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ አይሰማም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ከእንግዲህ ወዲህ በገና የሚመቱና የሚዘምሩ ሰዎች ድምፅ፥ እንቢልታንና መለከትንም የሚነፉ ሰዎች ድምፅ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ የማንኛውም ዕደ ጥበብ ብልሃተኛ ሰው ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይገኝም፤ የወፍጮ ድምጽም ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 የበገና ደርዳሪዎችና የሙዚቀኞች ድምፅ፥ የዋሽንት ነፊዎችና የእምቢልታ ነፊዎች ድምፅ፥ ዳግመኛ በአንቺ አይሰማም፤ ማንኛውንም ዐይነት የእጅ ጥበብ የሚሠራ ብልኀተኛ ሰው ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ አይገኝም፤ የወፍጮም ድምፅ ከእንግዲህ በአንቺ አይሰማም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 በገና የሚመቱና የሚዘምሩም ድምፅ እንቢልታንና መለከትንም የሚነፉ ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ የእጅ ጥበብም ሁሉ አንድ ብልሃተኛ እንኳ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይገኝም፤ የወፍጮ ድምጽም ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 በገና የሚመቱና የሚዘምሩም ድምፅ እንቢልታንና መለከትንም የሚነፉ ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፥ የእጅ ጥበብም ሁሉ አንድ ብልሃተኛ እንኳ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይገኝም፥ የወፍጮ ድምጽም ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፥

参见章节 复制




ራእይ 18:22
10 交叉引用  

ያ ሌሊት መካን ይሁን፤ እልልታም አይሰማበት።


ወደ አደባባይ የሚያወጡ በሮች ሲዘጉ፣ ወፍጮ ሟልጦ ድምፁ ሲላሽ፣ ሰው በወፍ ድምፅ ሲነሣ፣ ዝማሬው ሁሉ ሲዳከም፤


እንዲህም አለ፤ “አንቺ የተቀጠቀጥሽ የሲዶን ድንግል ሆይ፤ ከእንግዲህ ደስ አይበልሽ! “ተነሺ ወደ ቆጵሮስ ተሻገሪ፤ በዚያም እንኳ ሰላም አታገኚም።”


የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘እነሆ፤ በዐይናችሁ ፊት፣ በዘመናችሁም የደስታና የሐሤት ድምፅ፣ የሙሽራውንና የሙሽራዪቱን ድምፅ ከዚህ ስፍራ አስወግዳለሁ።’


የደስታንና የእልልታን ድምፅ፣ የሙሽራውንና የሙሽራዪቱን ድምፅ፣ የወፍጮን ድምፅና የመብራትን ብርሃን አስቀራለሁ።


የሐሤትና የደስታ ድምፅ፣ የሙሽራውና የሙሽራዪቱ ድምፅ፣ እንዲሁም፣ “ ‘ “እግዚአብሔር ቸር ነውና፤ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤” የሚል የምስጋናን መሥዋዕት ይዘው ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚመጡ ሰዎች ድምፅ ይሰማል፤ የምድሪቱን ምርኮ ቀድሞ እንደ ነበረ እመልሳለሁና፤’ ይላል እግዚአብሔር።


የደስታና የተድላን ድምፅ፣ የሙሽራና የሙሽራዪቱን ድምፅ ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም መንገዶች አጠፋለሁ፤ ምድሪቱ ባድማ ትሆናለችና።


ዘፈንሽን ጸጥ አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህም የበገናሽ ድምፅ አይሰማም።


ኢየሱስ ወደ ሹሙ ቤት እንደ ደረሰ እንቢልተኞችንና የሚንጫጫውን ሕዝብ አይቶ፣


跟着我们:

广告


广告