Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ራእይ 14:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ወይኑም ከከተማው ውጭ በወይን መጭመቂያ ውስጥ ተረገጠ፤ ከፍታው እስከ ፈረስ ልጓም የሚደርስ፣ ርዝመቱ ሦስት መቶ ኪሎ ሜትር ያህል ደም ከመጭመቂያው ወጣ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 የወይኑም መጥመቂያ ከከተማ ውጭ ተረገጠ፤ እስከ ፈረሶች ልጓም የሚደርስና እስከ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ምዕራፍ ድረስ የሚርቅ ደም ከመጥመቂያው ወጣ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ከከተማው ውጪ ባለው በወይን መጭመቂያም ተጨመቀ፤ ከመጭመቂያውም እስከ ፈረስ ልጓም ወደ ላይ ከፍ ያለና ሦስት መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት የሚደርስ ደም ወጥቶ ፈሰሰ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 የወይኑም መጥመቂያ ከከተማ ውጭ ተረገጠ፤ እስከ ፈረሶች ልጓምም የሚደርስ ደም ርቀቱ ሺህ ስድስት መቶ ምዕራፍ ሆኖ ከመጥመቂያው ወጣ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 የወይኑም መጥመቂያ ከከተማ ውጭ ተረገጠ፥ እስከ ፈረሶች ልጓምም የሚደርስ ደም ርቀቱ ሺህ ስድስት መቶ ምዕራፍ ሆኖ ከመጥመቂያው ወጣ።

参见章节 复制




ራእይ 14:20
12 交叉引用  

አህያውን በወይን ግንድ፣ ውርንጫውንም በምርጡ የወይን ሐረግ ቅርንጫፍ ላይ ያስራል፤ ልብሱን በወይን ጠጅ፣ መጐናጸፊያውንም በወይን ጭማቂ ያጥባል።


“ወጥተውም በእኔ ላይ ያመፁትን ሰዎች ሬሳ ያያሉ፤ የሚበሏቸው ትሎች አይሞቱም፤ የሚያቃጥላቸው እሳታቸው አይጠፋም፤ ለሰውም ዘር ሁሉ አስጸያፊ ይሆናሉ።”


“በውስጤ ያሉትን ጦረኞችህ ሁሉ፣ እግዚአብሔር ተቃወመ፤ ጕልማሶቼን ለማድቀቅ፣ ሰራዊት በላዬ ላይ ጠራ፤ ድንግሊቱን የይሁዳ ሴት ልጅ፣ እግዚአብሔር በወይን መጭመቂያ ውስጥ ረገጣት።


እስከ ተራሮች ባለው መንገድ ሁሉ፣ በሚፈስሰው ደምህ ምድሪቱን አርሳታለሁ፤ ሸለቆዎችም በሥጋህ ይሞላሉ።


ማጭዱን ስደዱ፤ መከሩ ደርሷልና፤ ኑ ወይኑን ርገጡ፤ የወይን መጭመቂያው ሞልቶ፣ ከጕድጓዶቹም ተርፎ ፈስሷልና፤ ክፋታቸው እንደዚህ ታላቅ ነው።”


የላሙንና የበጉን መንጋ ቅቤና ወተት፣ የሰቡትን በጎችና ፍየሎች፣ የባሳንን ምርጥ አውራ በግ፣ መልካም የሆነውንም ስንዴ፣ ማለፊያውንም የወይን ጠጅ።


ሬሳቸውም በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይጣላል፤ ይህች ከተማ ሰዶምና ግብጽ እየተባለች በምሳሌ የምትጠራውና የእነርሱም ጌታ የተሰቀለባት ናት።


跟着我们:

广告


广告