Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 68:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 በኢየሩሳሌም ስላለው ቤተ መቅደስህ፣ ነገሥታት እጅ መንሻ ያመጡልሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 አቤቱ፥ ኃይልህን እዘዝ፥ አቤቱ፥ ለእኛ የሠራኸውን አጽናው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 በዚህ ዐይነት በኢየሩሳሌም ስላለው መቅደስህ ነገሥታት መባን ያመጡልሃል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 እኔ ድሃና ቍስ​ለኛ ነኝ፤ የፊቴ፥ መድ​ኀ​ኒት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቀ​በ​ለኝ።

参见章节 复制




መዝሙር 68:29
18 交叉引用  

ከዚያም ለንጉሡ አንድ መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ፣ እጅግ ብዙ ቅመማ ቅመሞችና የከበሩ ድንጋዮች ሰጠችው፤ የሳባ ንግሥት ለንጉሥ ሰሎሞን ያበረከተችለትን ያን ያህል ብዛት ያለው ቅመማ ቅመም ከዚያ በኋላ ከቶ አልመጣም።


ከዚህም በቀር ለአምላኬ ቤት ካለኝ ፍቅር የተነሣ፣ ለዚህ ለተቀደሰ ቤት ከዚህ በፊት ከሰጠሁት በተጨማሪ፣ ለዚሁ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የግል ሀብቴ የሆነውን ወርቅና ብር እሰጣለሁ፤


ብዙዎችም ለእግዚአብሔር መባ ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ ለይሁዳ ንጉሥ ለሕዝቅያስም ውድ የሆኑ ገጸ በረከቶችን አመጡለት፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮም በአሕዛብ ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አለ።


ሕዝቅያስም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ የዳዊት ዘሮች መካነ መቃብር በሆነው ኰረብታም ተቀበረ። በሞተም ጊዜ ይሁዳ ሁሉና የኢየሩሳሌም ሕዝብ በሙሉ አከበሩት። ልጁ ምናሴም በእግሩ ተተካ።


እንዲሁም ለንጉሡ ደን ጠባቂ ለአሳፍ፣ በቤተ መቅደሱ አጠገብ ላለው ግንብ በሮች፣ ለከተማዪቱ ቅጥርና እኔም ለምገባበት ቤት ሠረገላ የሚሆን ዕንጨት እንዲሰጠኝ ደብዳቤ ይጻፍልኝ፤” መልካሚቱ የአምላኬ እጅ በእኔ ላይ ነበረችና ንጉሡም ፈቀደልኝ።


የጢሮስ ሴት ልጅ እጅ መንሻ ይዛ ትመጣለች፤ ሀብታሞችም ደጅ ይጠኑሻል።


ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ተሳሉ፤ ስእለቱንም አግቡ፤ በርሱ ዙሪያ ያሉ ሁሉ፣ አስፈሪ ለሆነው ለርሱ እጅ መንሻ ያምጡ።


በዚያ ጊዜ ለሰራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር፣ ረዣዥምና ቈዳው ከለሰለሰ፣ ከቅርብም ከሩቅም ከሚፈራ ሕዝብ፣ ኀያልና ቋንቋው ከማይገባ፣ ወንዞችም ምድሩን ከሚከፍሉት መንግሥት፣ ገጸ በረከት ይመጣለታል፤ ገጸ በረከቱም የሚመጣለት የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስም ወዳለበት ወደ ጽዮን ተራራ ነው።


跟着我们:

广告


广告