Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 64:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 አሸምቀው ንጹሑን ሰው ይነድፉታል፤ ድንገት ይነድፉታል፤ አይፈሩምም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እንደ ሰይፍ ምላሳቸውን አሰሉ፥ እንደ ፍላጻ መራራ ነገርን ለመወርወር፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እነርሱም ያለ ፍርሀት ንጹሑን ሰው ሸምቀው ይነድፉታል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 አንተ የመ​ረ​ጥ​ኸው በአ​ደ​ባ​ባ​ዮ​ች​ህም ለማ​ሳ​ደር የተ​ቀ​በ​ል​ኸው ብፁዕ ነው፤ አቤቱ፥ ከቤ​ትህ በረ​ከት ጠገ​ብን።

参见章节 复制




መዝሙር 64:4
14 交叉引用  

ከዚያም ዳዊት በኢየሩሳሌም ላሉት ሹማምቱ ሁሉ፣ “ተነሡ እንሽሽ፤ አለዚያ አንዳችንም ከአቤሴሎም እጅ ማምለጥ አንችልም፤ አሁኑኑ ከዚህ መውጣት አለብን፤ ካልሆነ ገሥግሦ መጥቶ ከያዘን እኛን ያጠፋናል፤ ከተማዪቱንም በሰይፍ ይመታታል” አላቸው።


ጠላቶቻችን ደግሞ፣ “በመካከላቸው ገብተን እስክንገድላቸውና ሥራውን እስክናስቆም ድረስ አያውቁም ወይም አያዩም” አሉ።


ደግሞም ለምን እንዲህ ትሉኛላችሁ? “ክፉዎች፣ እነሆ፤ ቀስታቸውን ገትረዋል፤ የቅኑን ሰው ልብ በጨለማ ለመንደፍ፣ ፍላጻቸውን በአውታሩ ላይ ደግነዋል።


አካሄዳቸውን አልቀየሩምና፣ እግዚአብሔርንም አልፈሩትምና፣ ከጥንት ጀምሮ በዙፋኑ ላይ ያለ አምላክ፣ ሴላ ሰምቶ ያዋርዳቸዋል።


የከበደህን ነገር በእግዚአብሔር ላይ ጣል፤ እርሱ ደግፎ ይይዝሃል፤ የጻድቁንም መናወጥ ከቶ አይፈቅድም።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤ ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትንሰራፋ።


እግዚአብሔር ግን በፍላጻው ይነድፋቸዋል፤ እነርሱም ድንገት ይቈስላሉ።


እንደ ዐውሎ ነፋስ ሊበታትነን የመጣውን፣ ምስኪኑን በስውር በመዋጥ የሚደሰተውን፣ የሰራዊት አለቃ ራስ፣ በገዛ ጦሩ ወጋህ።


የካህናት አለቆችና አገልጋዮቻቸውም ባዩት ጊዜ፣ “ስቀለው! ስቀለው!” እያሉ ጮኹ። ጲላጦስ ግን፣ “እናንተ ወስዳችሁ ስቀሉት፤ በእኔ በኩል ለክስ የሚያደርስ ወንጀል አላገኘሁበትም” አላቸው።


እርሱም፣ “ዳዊትን ከግድግዳው ጋራ አጣብቀዋለሁ” ብሎ በማሰብ ጦሩን ወረወረበት፤ ዳዊት ግን ሁለት ጊዜ ከፊቱ ዘወር አለ።


ሳኦልም ከግድግዳው ጋራ ሊያጣብቀው ጦሩን ወረወረበት፤ ነገር ግን ዳዊት ዘወር በማለቱ ሳኦል የወረወረው ጦር በግድግዳው ላይ ተሰካ። በዚያች ሌሊት ዳዊት ሸሽቶ አመለጠ።


跟着我们:

广告


广告