Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 55:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የሚዘልፈኝ ጠላት አይደለምና፤ ቢሆንማ ኖሮ በታገሥሁት ነበር፤ የሚጠላኝ፣ ራሱንም ቀና ቀና ያደረገብኝ ባላንጣ አይደለም፤ ቢሆንማ ከርሱ በተሸሸግሁ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በውስጧ ጥፋት አለ፤ ተንኰልና ሽንገላ ከአደባባይዋ አይርቁም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የሚሰድበኝ ጠላት አይደለም፤ ጠላት ቢሆንማ ኖሮ በታገሥኩ ነበር። የሚታበይብኝም ባለጋራ አይደለም፤ ባለጋራ ቢሆንማ ኖሮ ከፊቱ በተሰወርኩ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አቤቱ፥ የም​ስ​ጋና ስእ​ለት የም​ሰ​ጥህ ከእኔ ዘንድ ነው፤

参见章节 复制




መዝሙር 55:12
7 交叉引用  

በጭንቀቴ ደስ የሚላቸው፣ ይፈሩ፤ ግራም ይጋቡ፤ በእኔ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ፣ ዕፍረትንና ውርደትን ይከናነቡ።


እኔ፣ “ጠላቶቼ በእኔ ላይ ደስ አይበላቸው፤ እግሬም ሲንሸራተት፣ በላዬ አይኵራሩብኝ” ብያለሁና።


እንጀራዬን የበላ፣ የምተማመንበትም የቅርብ ወዳጄ፣ ተረከዙን አነሣብኝ።


መጥረቢያ በሚቈርጥበት ሰው ላይ ይኵራራልን? መጋዝስ በሚስበው ላይ ይታበያልን? በትር በሚያነሣው ሰው ላይ ራሱን እንደሚነቀንቅ፣ ዘንግም ራሱን ዕንጨት እንዳልሆነ አድርጎ እንደሚኵራራ ነው።


“ስለ ሁላችሁ መናገሬ አይደለም፤ የመረጥኋቸውን ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን፣ ‘እንጀራዬን የሚበላ ተረከዙን አነሣብኝ’ የሚለው የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው።


跟着我们:

广告


广告