Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 52:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከበጎ ነገር ይልቅ ክፋትን፣ ጽድቅን ከመናገር ይልቅ ዐመፃን ወደድህ። ሴላ

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ኃያል ሆይ፥ በክፋት ለምን ትኩራራለህ? ሁልጊዜስ በመተላለፍ?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ከደግነት ይልቅ ክፋትን፥ ከእውነት ይልቅ ሐሰትን ትመርጣለህ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሁሉ ተካ​ክሎ በአ​ን​ድ​ነት በደለ፤ አንድ ስንኳ በጎ ነገ​ርን የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት የለም።

参见章节 复制




መዝሙር 52:3
10 交叉引用  

ከታላቅ ክብሩ ሊያዋርዱት፣ ይህን አንድ ነገር ወጠኑ፤ ሐሰት ባለበት ነገር ደስ ይሰኛሉ፤ በአፋቸው ይመርቃሉ፤ በልባቸው ግን ይራገማሉ። ሴላ


ክፉ ሰው ክፋትን አጥብቆ ይመኛል፤ ባልንጀራውም ከርሱ ዘንድ ርኅራኄን አያገኝም።


“ሕዝቤ ቂሎች ናቸው፤ እኔን አያውቁኝም። ማስተዋል የጐደላቸው፣ መረዳትም የማይችሉ ልጆች ናቸው። ክፋትን ለማድረግ ጥበበኞች፣ መልካም መሥራት ግን የማያውቁ።”


ምላሳቸው የሚገድል ቀስት ነው፤ በሽንገላ ይናገራል፤ ሁሉም ከባልንጀራው ጋራ በሰላም ይናገራል፤ በልቡ ግን ያደባበታል።


መልካሙን ጠላችሁ፤ ክፉውንም ወደዳችሁ፤ የሕዝቤን ቈዳ ገፈፋችሁ፤ ሥጋቸውንም ከዐጥንቶቻቸው ለያችሁ፤


እናንተ የአባታችሁ የዲያብሎስ ናችሁ፤ የአባታችሁንም ፍላጎት ለመፈጸም ትሻላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበር፤ በርሱ ዘንድ እውነት ስለሌለ በእውነት አልጸናም፤ እርሱ ሐሰተኛ፣ የሐሰትም አባት በመሆኑ ሐሰትን ሲናገር፣ የሚናገረው ከራሱ አፍልቆ ነው፤


የእግዚአብሔርን እውነት በሐሰት ለወጡ፤ በፈጣሪ ፈንታ ፍጡር አመለኩ፤ አገለገሉም፤ ፈጣሪም ለዘላለም የተመሰገነ ነው። አሜን።


ከዳተኞች፣ ችኵሎች፣ በከንቱ በትዕቢት የተወጠሩ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወድዱ ይሆናሉና።


ውሾች፣ አስማተኞች፣ ሴሰኞች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ ውሸትን የሚወድዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።


跟着我们:

广告


广告