16 እንደ ምናምንቴዎች አፌዙብኝ፤ ጥርሳቸውንም አፋጩብኝ።
16 ፈተኑኝ በሣቅም ዘበቱብኝ፥ ጥርሳቸውንም በእኔ ላይ አንቀጫቀጩ።
16 ክፉዎች ሰዎች እንደሚያደርጉት እነርሱ በክፋት አፌዙብኝ፤ በእኔም ላይ ጥርሳቸውን አፋጩ።
በቍጣው ሰነጠቀኝ፤ በጥላቻው አስጨነቀኝ፣ ጥርሱን ነከሰብኝ፤ ባላጋራዬ ክፉ ዐይኑን ተከለብኝ።
ክፉዎች በጻድቃን ላይ ያሤራሉ፤ ጥርሳቸውንም ያፋጩባቸዋል።
ጠላቶችሽ ሁሉ በአንድ ላይ፣ አፋቸውን በኀይል ከፈቱ፤ ጥርሳቸውን እያፏጩ አሾፉ፤ እንዲህም አሉ፤ “ውጠናታል፤ የናፈቅነው ጊዜ ይህ ነበር፤ ኖረንም ልናየው በቃን።”
አይሁድም ኢየሱስን ከቀያፋ ወደ ሮማዊው ገዥ ግቢ ይዘውት ሄዱ፤ ጊዜውም ማለዳ ነበር። አይሁድም ፋሲካን መብላት እንዲችሉ፣ ላለመርከስ ወደ ገዥው ግቢ አልገቡም።
በሸንጎው ስብሰባ ላይ የነበሩትም ይህን በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቈጡ፤ ጥርሳቸውንም አፋጩበት።
ስለዚህ በዓሉን ግፍና ክፋት በሞላበት እርሾ፣ በአሮጌ እርሾ ሳይሆን፣ እርሾ በሌለበት ቂጣ በቅንነትና በእውነት እናክብር።