Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 33:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔር አምላኩ የሆነው ሕዝብ፣ ለርስቱ የመረጠውም ወገን፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ጌታ አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እግዚአብሔር አምላኩ የሆነለትና እግዚአብሔር የራሱ አድርጎ የመረጠው ሕዝብ የተባረከ ነው!

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ሕይ​ወ​ትን የሚ​ፈ​ቅድ ሰው ማን ነው? በጎ ዘመ​ን​ንም ለማ​የት የሚ​ወ​ድድ ማን ነው?

参见章节 复制




መዝሙር 33:12
17 交叉引用  

በእስራኤል ሰላማዊና ታማኝ ከሆኑ ሰዎች መካከል አንዷ እኔ ነኝ፤ አንተ በእስራኤል እናት የሆነችውን ከተማ ለማጥፋት ትሻለህ፤ የእግዚአብሔርን ርስት ለመዋጥ የፈለግኸው ለምንድን ነው?”


እግዚአብሔር ያዕቆብን ለራሱ፣ እስራኤልንም ውድ ንብረቱ አድርጎ መርጧልና።


ብፁዕ ነው፤ ይህ ባርኮት ገንዘቡ የሆነ ሕዝብ፤ ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ሕዝብ።


ሕዝብህን አድን፤ ርስትህንም ባርክ፤ እረኛ ሁናቸው፤ ለዘላለሙም ዐቅፈህ ያዛቸው።


ብፁዕ ነው፤ አንተ የመረጥኸው፣ ወደ ራስህ ያቀረብኸው፣ በአደባባይህም ያኖርኸው፤ ከተቀደሰው መቅደስህ፣ ከቤትህም በረከት እንረካለን።


“አቤቱ ጌታ ሆይ፤ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፣ ጌታ ከእኛ ጋራ ይሂድ፤ ይህ ዐንገተ ደንዳና ሕዝብ ቢሆንም እንኳ፣ ክፋታችንንና ኀጢአታችንን ይቅር በል፤ እንደ ርስትህም አድርገህ ውሰደን።”


እኔ ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራ፤ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ። አበረታሃለሁ፤ እረዳሃለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ እጄ ደግፌ እይዝሃለሁ።


የያዕቆብ ዕድል ፈንታ የሆነው ግን እንደ እነዚህ አይደለም፤ እርሱ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነውና፤ እስራኤልም የርስቱ ነገድ ነው። ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።


እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ እንድትሄዱና ፍሬ እንድታፈሩ፣ ፍሬያችሁም እንዲኖር ሾምኋችሁ። ስለዚህም አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል።


በፊቱ ቅዱስና እንከን አልባ እንድንሆን ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በርሱ መርጦናልና። በፍቅር፣


የእግዚአብሔር ድርሻ የገዛ ሕዝቡ፣ ያዕቆብ የተለየ ርስቱ ነውና።


ብፁዕ ነህ፤ አንተ እስራኤል ሆይ፤ እግዚአብሔር ያዳነው ሕዝብ፣ እንደ አንተ ያለ ማን አለ? እርሱ ጋሻህና ረዳትህ፣ የክብርህም ሰይፍ ነው። ጠላቶችህ በፍርሀት ከፊትህ ያፈገፍጋሉ፤ አንተም የማምለኪያ ኰረብታቸውን መረማመጃ ታደርጋለህ።”


እርሱም ከክፋት ሊቤዠን፣ መልካም የሆነውን ለማድረግ የሚተጋውን የርሱ የሆነውን ሕዝብም ለራሱ ያነጻ ዘንድ ራሱን ስለ እኛ ሰጥቷል።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ የተቀደሰ ሕዝብ፣ እግዚአብሔር ገንዘቡ ያደረገው ሕዝብ ናችሁ።


跟着我们:

广告


广告