Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 142:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ስምህን አመሰግን ዘንድ፣ ነፍሴን ከእስር አውጣት፤ ከምታደርግልኝም በጎ ነገር የተነሣ፣ ጻድቃን በዙሪያዬ ይሰበሰባሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እጅግ ተቸግሬአለሁና ጩኸቴን አድምጥ፥ በርትተውብኛልና ከሚያሳድዱኝ አድነኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 አመሰግንህ ዘንድ ከእስራቴ አውጣኝ፤ ለእኔ ያደረግኸውን ያንተን የቸርነት ሥራ በሚያዩበት ጊዜ ሕዝብህ በዙሪያዬ ይሰበሰባሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አቤቱ፥ ፈጥ​ነህ ስማኝ፥ ሰው​ነቴ አል​ቃ​ለች፤ ፊት​ህ​ንም ከእኔ አት​መ​ልስ፥ ወደ ጕድ​ጓ​ድም እን​ደ​ሚ​ወ​ርዱ አል​ሁን።

参见章节 复制




መዝሙር 142:7
20 交叉引用  

ነፍሴ ሆይ፤ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ፤ እግዚአብሔር መልካም አድርጎልሻልና።


ሕያው እንድሆን፣ ቃልህንም እንድጠብቅ፣ ለአገልጋይህ መልካም አድርግ።


ቃልህን ተስፋ አድርጌአለሁና፣ የሚፈሩህ እኔን አይተው ደስ ይበላቸው።


ቸርነቱ ታምኛለሁና፣ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ።


ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤ ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር ልመና አቀርባለሁ።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ስለ ስምህ ሕያው አድርገኝ፤ በጽድቅህም ነፍሴን ከመከራ አውጣት።


እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን መሰወሪያ አድርጌአለሁና፣ ከጠላቶቼ አድነኝ።


ለተበደሉት የሚፈርድ፣ ለተራቡት ምግብን የሚሰጥ እርሱ ነው፤ እግዚአብሔር እስረኞችን ከእስራት ያወጣል፤


ለጠላት አሳልፈህ አልሰጠኸኝም፤ ነገር ግን እግሮቼን ሰፊ ቦታ ላይ አቆምሃቸው።


ነፍሴ በእግዚአብሔር ተመካች፤ ትሑታንም ይህን ሰምተው ሐሤት ያደርጋሉ።


መልካሙን ስለ ተከተልሁ፣ በበጎ ፈንታ ክፉ የሚመልሱልኝ ከሰሱኝ።


ይህን ስታደርግልኝ፣ በጽዮን ሴት ልጅ ደጅ፣ ምስጋናህን ዐውጃለሁ፤ በማዳንህም ሐሤት አደርጋለሁ።


ጠላቶቼ ወደ ኋላ በተመለሱ ጊዜ፣ ተሰነካክለው ከፊትህ ይጠፋሉ፤


የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድኾች ወንጌልን እንድሰብክ፣ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና። ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፣ ለምርኮኞች ነጻነትን፣ ለእስረኞች መፈታትን እንዳውጅ ልኮኛል።


እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አስወግዶ አስነሣው፤ ሞት ይዞ ሊያስቀረው አልቻለምና።


በትዕግሥት የጸኑትን የተባረኩ አድርገን እንደምንቈጥር ታውቃላችሁ፤ ኢዮብ እንዴት ታግሦ እንደ ጸና ሰምታችኋል፤ ጌታም በመጨረሻ ያደረገለትን አይታችኋል። ጌታ እጅግ ርኅሩኅና መሓሪ ነው።


跟着我们:

广告


广告