84 የባሪያህ ዕድሜ ስንት ቢሆን ነው? ታዲያ፣ በሚያሳድዱኝ ላይ የምትፈርደው መቼ ይሆን?
84 የባርያህ ዘመኖች ስንት ናቸው? በሚያሳድዱኝስ ላይ መቼ ትፈርድልኛለህ?
84 እኔ አገልጋይህ እስከ መቼ ልቈይ? የሚያሳድዱኝንስ የምትቀጣቸው መቼ ነው?
እግዚአብሔር ሆይ፤ በመዓትህ ተነሥ፤ በቍጣ በተነሡብኝ ላይ ተነሥ፤ አምላኬ ሆይ፤ ንቃ፤ ትእዛዝም አስተላልፍ!
ጥበብን የተሞላ ልብ ይኖረን ዘንድ፣ ዕድሜያችንን መቍጠር አስተምረን።