Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 119:144 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

144 ምስክርነትህ ለዘላለም የጽድቅ ምስክርነት ነው፤ በሕይወት እኖር ዘንድ ማስተዋልን ስጠኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

144 ምስክርህ ለዘለዓለም ጽድቅ ነው፥ እንዳስተውል አድርገኝ፥ በሕይወትም አኑረኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

144 ሥርዓትህ ዘወትር ትክክል ነው፤ በሕይወት ለመኖር እንድችል ማስተዋልን ስጠኝ።

参见章节 复制




መዝሙር 119:144
23 交叉引用  

ምስክርነትህን በጽድቅ አዘዝህ፤ እጅግ አስተማማኝም ነው።


እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ቅርብ ነህ፤ ትእዛዞችህም ሁሉ እውነት ናቸው።


ለዘላለም እንደ መሠረትሃቸው፣ ከጥንት ምስክርነትህ ተረድቻለሁ።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ጩኸቴ ከፊትህ ይድረስ፤ እንደ ቃልህም ማስተዋልን ስጠኝ።


ሕያው እንድሆን፣ ቃልህንም እንድጠብቅ፣ ለአገልጋይህ መልካም አድርግ።


ሕግህን እንድጠብቅ፣ በፍጹም ልቤም እንድታዘዘው፣ ማስተዋልን ስጠኝ።


በትእዛዞችህ አምናለሁና፣ በጎ ማስተዋልንና ዕውቀትን አስተምረኝ።


እጆችህ ሠሩኝ፤ አበጃጁኝም፤ ትእዛዞችህን እንድማር ማስተዋልን ስጠኝ።


እግዚአብሔርን መፍራት ንጹሕ ነው፤ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል። የእግዚአብሔር ፍርድ የታመነ፣ ሁለንተናውም ጻድቅ ነው።


የጻድቃን ከንፈሮች ብዙዎችን ያንጻሉ፤ ቂሎች ግን በልበ ቢስነት ይሞታሉ።


አባቴ እንዲህ ሲል አስተማረኝ፤ “ቃሌን በሙሉ በልብህ ያዝ፤ ትእዛዜንም ጠብቅ፤ በሕይወት ትኖራለህ።


ትእዛዜን ጠብቅ፤ በሕይወት ትኖራለህ፤ ትምህርቴንም እንደ ዐይንህ ብሌን ተንከባከበው።


ጫፎቿ ሲደርቁ ይሰበራሉ፤ ሴቶችም መጥተው ይማግዷቸዋል። ማስተዋል የሌለው ሕዝብ ስለ ሆነ፣ ፈጣሪው አይራራለትም፤ ያበጀውም አይምረውም።


“ሕዝቤ ቂሎች ናቸው፤ እኔን አያውቁኝም። ማስተዋል የጐደላቸው፣ መረዳትም የማይችሉ ልጆች ናቸው። ክፋትን ለማድረግ ጥበበኞች፣ መልካም መሥራት ግን የማያውቁ።”


ብዙዎች ይነጻሉ፤ ይጠራሉ፤ እንከን አልባም ይሆናሉ፤ ክፉዎች ግን በክፋታቸው ይጸናሉ፤ ከክፉዎች አንዳቸውም አያስተውሉም፤ ጠቢባን ግን ያስተውላሉ።


ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቷል። ዕውቀትን ስለ ናቃችሁ፣ እኔም ካህናት እንዳትሆኑ ናቅኋችሁ፤ የአምላካችሁን ሕግ ስለ ረሳችሁ፣ እኔም ልጆቻችሁን እረሳለሁ።


የእግዚአብሔርን መንግሥት ቃል ሰምቶ ከማያስተውል ከማንኛውም ሰው ልብ ውስጥ ክፉው መጥቶ የተዘራውን ዘር ይነጥቃል። ይህ እንግዲህ በመንገድ ዳር የተዘራው ዘር ነው።


እውነት እላችኋለሁ፤ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ ሕግ ሁሉ ይፈጸማል እንጂ ከሕግ አንዲት ፊደል ወይም አንዲት ነጥብ እንኳ አትሻርም።


እውነተኛ አምላክ የሆንኸውን አንተንና የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።


በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት እግዚአብሔር የክብሩን ዕውቀት ብርሃን ይሰጠን ዘንድ፣ “በጨለማ ብርሃን ይብራ” ያለው እግዚአብሔር ብርሃኑን በልባችን አብርቷልና።


跟着我们:

广告


广告