122 ለባሪያህ በጎነት ዋስትና ሁን፤ እብሪተኞች እንዲጨቍኑኝ አትፍቀድላቸው።
122 ባርያህን በመልካም ጠብቀው፥ ትዕቢተኞችም አይጋፉኝ።
122 የእኔን የአገልጋይህን ደኅንነት አረጋግጥ፤ እብሪተኞች እንዲያጠቁኝ አታድርግ።
ስለ ልጁ ደኅንነት እኔ ራሴ ኀላፊ ነኝ፤ ስለ እርሱም በግል ተጠያቂ እሆናለሁ፤ እርሱንም በደኅና መልሼ ባላመጣውና እዚህ በፊትህ ባላቆመው ለዘላለም በደለኛው እኔ ልሁን።
“አምላክ ሆይ፤ አንተ ተያዥ ሁነኝ፤ ከአንተ ሌላ ዋስ የሚሆነኝ ማን አለ?
ከትእዛዞችህ የሳቱትን፣ እብሪተኞችንና ርጉሞችን ትገሥጻለህ።
የትዕቢተኛ እግር በላዬ አይምጣ፤ የክፉውም ሰው እጅ አያሳድደኝ።
እንደ ጨረባ፣ እንደ ሽመላም ተንጫጫሁ፤ እንደ ርግብ አልጐመጐምሁ፤ ዐይኖቼ ወደ ሰማይ በመመልከት ደከሙ፤ ጌታ ሆይ፤ ተጨንቄአለሁና ታደገኝ!”
ከዚህ መሐላ የተነሣ፣ ኢየሱስ ለተሻለ ኪዳን ዋስ ሆኗል።