Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 102:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፤ እነርሱም ወዲያ ይጣላሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 አቤቱ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ትኖራለህ፤ እነርሱ እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ እንደ መጐናጸፊያ ትለውጣቸዋለህ፤ ይወገዱማል።

参见章节 复制




መዝሙር 102:26
14 交叉引用  

ሕዝቅያስም እንዲህ ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ “በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በምድር መንግሥታት ሁሉ ላይ አንተ ብቻ አምላክ ነህ፤ ሰማይንና ምድርንም ፈጥረሃል።


“ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ የት ነበርህ? በርግጥ የምታስተውል ከሆንህ ንገረኝ።


እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ለዘላለም በዙፋንህ ተቀምጠሃል፤ ስምህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።


እግዚአብሔርም ሙሴን፣ “እኔ፣ ያለሁና የምኖር ነኝ፤ ስለዚህም ለእስራኤል ልጆች፣ ‘ያለና የሚኖር ልኮኛል’ ብለህ ንገራቸው” አለው።


የሰማይ ከዋክብት ሁሉ ይሟሽሻሉ፤ ሰማይ እንደ ብራና ይጠቀለላል፤ የከዋክብት ሰራዊት ሁሉ፣ ጠውልጎ እንደ ረገፈ የወይን ቅጠል፣ ደርቆም እንደ ወደቀ የበለስ ቅጠል ይሆናሉ።


ዐይኖቻችሁን ወደ ሰማያት አንሡ፤ ወደ ታች ወደ ምድርም ተመልከቱ፤ ሰማያት እንደ ጢስ በንነው ይጠፋሉ፤ ምድር እንደ ልብስ ታረጃለች፤ ነዋሪዎቿም እንደ ዐሸን ፈጥነው ይረግፋሉ፤ ማዳኔ ግን ለዘላለም ይኖራል፤ ጽድቄም መጨረሻ የለውም።


“እነሆ፤ እኔ፣ አዲስ ሰማያትንና አዲስ ምድርን እፈጥራለሁ፤ ያለፉት ነገሮች አይታሰቡም፤ አይታወሱም።


“እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር በፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፣ የእናንተና የዘራችሁ ስም እንደዚሁ ጸንቶ ይኖራል” ይላል እግዚአብሔር፤


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ፈጽሞ አያልፍም።


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።


ፍጥረት ሁሉ ለከንቱነት ተዳርጓል፤ ይኸውም በራሱ ምርጫ ሳይሆን፣ ለተስፋ እንዲገዛ ካደረገው ከፈቃዱ የተነሣ ነው።


ከዚህ በኋላ ታላቅ ነጭ ዙፋንና በርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ። ምድርና ሰማይ ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም አልተገኘላቸውም።


ከዚህ በኋላ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር አየሁ፤ የመጀመሪያው ሰማይና የመጀመሪያዪቱ ምድር ዐልፈዋልና፤ ባሕርም ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።


跟着我们:

广告


广告