Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 9:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ፌዘኛን የሚገሥጽ ሁሉ ስድብን በራሱ ላይ ያመጣል፤ ክፉውን ሰው የሚዘልፍ ሁሉ ውርደት ያገኘዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ፌዘኛን የሚገሥጽ ለራሱ ስድብን ይቀበላል፥ ክፉንም የሚዘልፍ ኃፍረት ይገጥመዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ትዕቢተኛን ሰው ብታርመው ስድብን ታተርፋለህ፤ ክፉውን ሰው ብትገሥጸው ጒዳት ይደርስብሃል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ክፉዎችን የሚያስተምር ለራሱ ውርደትን ይቀበላል፥ ኃጥእንም የሚገሥጽ ራሱን ያዋርዳል።

参见章节 复制




ምሳሌ 9:7
13 交叉引用  

አክዓብ ኤልያስን ባየው ጊዜ፤ “እስራኤልን የምታውክ አንተ ነህን?” አለው።


አክዓብም ኤልያስን፣ “ጠላቴ ሆይ አገኘኸኝን?” አለው። ኤልያስም መልሶ እንዲህ አለው፤ “በእግዚአብሔር ፊት የተጠላውን ነገር ለማድረግ ራስህን ሸጠሃልና አዎን አግኝቼሃለሁ።


ከዚያም የክንዓና ልጅ ሴዴቅያስ ወጥቶ ሚክያስን በጥፊ መታውና፣ “ለመሆኑ የእግዚአብሔር መንፈስ በየት በኩል ዐልፎኝ ነው አንተን ያናገረህ?” አለው።


ከዚያም፣ ‘ንጉሡ፣ ይህን ሰው እስር ቤት አስገቡት፤ በደኅና እስክመለስም ድረስ፣ ከደረቅ እንጀራና ከውሃ በቀር ሌላ እንዳትሰጡት’ ብሏል በሏቸው” አለ።


እነርሱ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ እስኪነሣሣና ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ በእግዚአብሔር መልእክተኞች ላይ ተሣለቁ፤ ቃሉን ናቁ፤ ነቢያቱንም አቃለሉ።


“እነሆ፤ እግዚአብሔር የሚገሥጸው ሰው ብፁዕ ነው፤ ስለዚህ ሁሉን ቻይ አምላክ ተግሣጽ አትናቅ።


ጠቢብ ልጅ የአባቱን ምክር በማስተዋል ይሰማል፤ ፌዘኛ ግን ተግሣጽን አያዳምጥም።


ፌዘኛ መታረምን አይወድድም፤ ጠቢባንንም አያማክርም።


ከሞኝ ጋራ አትነጋገር፤ የቃልህን ጥበብ ያንኳስሳልና።


ነገር ግን ሕዝቡ ዝም አለ፤ ምንም መልስ አልሰጠም፤ ንጉሡ፣ “መልስ እንዳትሰጡ” ሲል አዝዞ ነበርና።


跟着我们:

广告


广告