Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 6:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እነዚህ ትእዛዞች መብራት ናቸውና፤ ይህችም ትምህርት ብርሃን፣ የተግሣጽ ዕርምትም የሕይወት መንገድ ናት፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ትእዛዝ መብራት፥ ትምህርትም ብርሃን ነውና፥ የተግሣጽም ዘለፋ የሕይወት መንገድ ነውና፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 የእግዚአብሔር ትእዛዝ፥ እንደ መብራት፥ ትምህርቱም እንደ ብርሃን ያበሩልሃል፤ ተግሣጹ እንዴት መኖር እንደሚቻል ያስተምራል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ትእዛዝ መብራት፥ ሕግም ብርሃን ነውና፥ ትምህርትና ተግሣጽም የሕይወት መንገድ ነውና፥

参见章节 复制




ምሳሌ 6:23
22 交叉引用  

እርሱ ግን ፈቃደኛ አልሆነም፤ እንዲህም አላት፤ “ጌታዬ ያለውን ሁሉ በኀላፊነት ስለ ሰጠኝ፣ በቤቱ ውስጥ ስላለው ሁሉ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም።


ሕግህ ለእግሬ መብራት፣ ለመንገዴም ብርሃን ነው።


የቃልህ ትርጓሜ ያበራል፤ አላዋቂዎችንም አስተዋዮች ያደርጋል።


ጻድቅ ሰው ይቅጣኝ፤ ይህ በጎነት ነው፤ ይገሥጸኝም፤ በራሴ ላይ እንደሚፈስስ ዘይት ነው፤ ራሴም ይህን እንቢ አይልም። ጸሎቴ ግን በክፉዎች ተግባር ላይ ነው።


የእግዚአብሔር ሕግጋት ትክክል ናቸው፤ ልብን ደስ ያሰኛሉ። የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፤ ዐይንን ያበራል።


ተግሣጽን ነቅቶ የሚጠብቅ የሕይወትን መንገድ ያሳያል፤ ዕርምትን የማይቀበል ግን ሌሎችን ወደ ስሕተት ይመራል።


ወደ ሲኦል ከመውረድ እንዲድን፣ የሕይወት መንገድ ጠቢቡን ሰው ወደ ላይ ትመራዋለች።


ሕይወት ሰጪ የሆነውን ተግሣጽ የሚሰማ፣ በጠቢባን መካከል ይኖራል።


የተግሣጽ በትር ጥበብን ታጐናጽፋለች፤ መረን የተለቀቀ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል።


ለሚያቅፏት የሕይወት ዛፍ ናት፤ የሚይዟትም ይባረካሉ።


ምክርን አጥብቀህ ያዛት፤ አትልቀቃት፤ ጠብቃት፤ ሕይወትህ ናትና።


አባቴ እንዲህ ሲል አስተማረኝ፤ “ቃሌን በሙሉ በልብህ ያዝ፤ ትእዛዜንም ጠብቅ፤ በሕይወት ትኖራለህ።


እንዲህም ትላለህ፤ “ምነው ተግሣጽን ጠላሁ! ልቤስ ምነው መታረምን ናቀ!


ልቧ ወጥመድና አሽክላ፣ እጆቿም እግር ብረት የሆኑ፣ ከሞት የከፋችዋን ሴት አገኘሁ፤ አምላክን ደስ የሚያሰኝ ከእጇ ያመልጣል፤ ኀጢአተኛውን ግን አጥምዳ ትይዘዋለች።


የሞኞችን መዝሙር ከመስማት፣ የጠቢባንን ሰዎች ተግሣጽ መስማት ይሻላል።


ወደ ሕጉና ወደ ምስክር ቃሉ ሂዱ! እነርሱም እንዲህ ያለውን ቃል ባይናገሩ የንጋት ብርሃን አይበራላቸውም።


“በተጨማሪም ለዚህ ሕዝብ እንዲህ በል፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ የሕይወትን መንገድና የሞትን መንገድ በፊታችሁ አድርጌአለሁ፤


ሰው ቢጠብቀው ኖሮ በሕይወት የሚኖርበትን ሥርዐቴን ሰጠኋቸው፤ ሕጌንም አስታወቅኋቸው።


“ ‘ወንድምህን በልብህ አትጥላው፤ የበደሉ ተካፋይ እንዳትሆን ባልንጀራህን በግልጽ ገሥጸው።


እንግዲያስ ትንቢታዊው ቃል ይበልጥ ተረጋግጦልናል፤ ሌሊቱ እስኪነጋና የንጋት ኮከብ በልባችሁ እስኪበራ ድረስ፣ በጨለማ ስፍራ ለሚበራ መብራት ጥንቃቄ እንደሚደረግ እናንተም ለዚህ ቃል ብትጠነቀቁ መልካም ታደርጋላችሁ።


እንግዲህ ከየት እንደ ወደቅህ ዐስብ፤ ንስሓ ገብተህ ቀድሞ ታደርገው የነበረውን ነገር አድርግ፤ ንስሓ ካልገባህ፣ መጥቼ መቅረዝህን ከቦታው እወስድብሃለሁ።


跟着我们:

广告


广告