Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 5:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ምንጮችህ ተርፈው ወደ ሜዳ፣ ወንዞችህስ ወደ አደባባይ ሊፈስሱ ይገባልን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ምንጮችህ ወደ ሜዳ፥ ወንዞችህ ወደ አደባባይ ይፈስሳሉን?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ማንኛዋም ሴት የምትጠጣበት የውሃ ምንጭ አትሁን።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ከምንጮችህ ውኆች ወደ ሜዳ አይፍሰሱ። ውኃዎችም ወደ አደባባዮች አይሂዱ፥

参见章节 复制




ምሳሌ 5:16
13 交叉引用  

ርብቃንም እንዲህ ብለው መረቋት፤ “እኅታችን ሆይ፤ እልፍ አእላፋት ሁኚ፤ ዘርሽ የጠላቶቹን ደጆች ይውረስ”።


እነሆ፤ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፤ የማሕፀንም ፍሬ ከቸርነቱ የሚገኝ ነው።


ሚስትህ በቤትህ፣ እንደሚያፈራ ወይን ናት፤ ወንዶች ልጆችህ በማእድህ ዙሪያ፣ እንደ ወይራ ተክል ናቸው።


እግዚአብሔርን በጉባኤ አመስግኑት፤ ከእስራኤል ምንጭ የተገኛችሁ እግዚአብሔርን አመስግኑ።


ከገዛ ማጠራቀሚያህ ውሃ፣ ከገዛ ጕድጓድህም የሚፈልቀውን ውሃ ጠጣ።


ለአንተ ብቻ ይሁኑ፤ ባዕዳን አይጋሩህ።


ምንጭህ ቡሩክ ይሁን፤ በልጅነት ሚስትህም ደስ ይበልህ።


“የስርቆት ውሃ ይጣፍጣል፤ ተሸሽገው የበሉት ምግብ ይጥማል።”


እኅቴ ሙሽራዬ፤ የታጠረ የአትክልት ቦታ፣ ዙሪያውን የተከበበ ምንጭ፣ የታተመም ፏፏቴ ነሽ።


አንቺ የአትክልት ቦታ ፏፏቴ፣ ከሊባኖስ የሚወርድ፣ የፈሳሽ ውሃ ጕድጓድ ነሽ።


በምድረ በዳ ሲመራቸው አልተጠሙም ነበር፤ ውሃ ከዐለት አፈለቀላቸው፤ ዐለቱን ሰነጠቀ፤ ውሃውም በኀይል ፈልቆ ወጣ።


ስለዚህ እስራኤል ብቻውን ያለ ሥጋት ይኖራል፤ የሰማያት ጠል በሚወርድበት፣ እህልና የወይን ጠጅ ባለበት ምድር፣ የያዕቆብን ምንጭ የሚነካው የለም።


እርሱም ሠላሳ ወንዶችና ሠላሳ ሴቶች ልጆች ነበሩት። ሴቶች ልጆቹንም ከጐሣው ውጭ ለሆኑ ሰዎች ዳራቸው፤ ከጐሣው ውጭ የሆኑ ሠላሳ ልጃገረዶች አምጥቶ ከወንዶች ልጆቹ ጋራ አጋባቸው። ኢብጻን በእስራኤል ላይ ሰባት ዓመት ፈራጅ ሆነ።


跟着我们:

广告


广告