Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 4:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፤ ሰውን ካላሰናከሉ እንቅልፍ በዐይናቸው አይዞርም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፥ ካላሰናከሉም እንቅልፋቸው ይወገዳልና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ክፉ ነገር ካላደረጉ ዕረፍት አይኖራቸውም፤ በሰው ላይ ጒዳት ካላደረሱ ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፍ አጥተው ያድራሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፥ ከዐይናቸው እንቅልፋቸው ይወገዳል አይተኙምም።

参见章节 复制




ምሳሌ 4:16
13 交叉引用  

ከአንደበቱ የሚወጣው የክፋትና የተንኰል ቃል ነው፤ ማስተዋልንና በጎ ማድረግን ትቷል።


በመኝታው ላይ ክፋትን ያውጠነጥናል፤ ራሱን በጎ ባልሆነ መንገድ ይመራል፤ ክፋትንም አያርቅም።


እግራቸው ወደ ኀጢአት ይቸኵላል፤ ደም ለማፍሰስም ፈጣኖች ናቸው።


ክፉ በመሥራት ደስ የሚላቸው፣ በክፋት ጐዳና ሐሤት የሚያደርጉ፣


ከዚያ አትድረስ፤ አትጓዝበት፤ ሽሸው፤ መንገድህን ይዘህ ሂድ፤


ክፉዎች ግን ማዕበሉ ጭቃና ጕድፍ እንደሚያወጣ፣ ጸጥ ማለት እንደማይችል፣ እንደሚናወጥ ባሕር ናቸው።


“እያንዳንዱ ወንድም አታላይ፣ ባልንጀራም ሁሉ ሐሜተኛ ስለ ሆነ፣ ወንድም ከወንድሙ ይጠንቀቅ፤ ባልንጀራም በጓደኛው አይታመን።


ክፉ ለመሥራት ለሚያቅዱ፣ በመኝታቸው ሳሉ ተንኰል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው! ሲነጋ በማለዳ ይፈጽሙታል፤ የሚያደርጉበት ኀይል በእጃቸው ነውና።


እጆቹ ክፉ ለማድረግ ሠልጥነዋል፤ ገዥው እጅ መንሻ ይፈልጋል፤ ፈራጁ ጕቦ ይቀበላል፤ ኀይለኞች ያሻቸውን ያስፈጽማሉ፤ ሁሉም አንድ ላይ ያሤራሉ።


በነጋም ጊዜ፣ የሕዝብ ሽማግሌዎች፣ የካህናት አለቆችና ጸሐፍት ተሰበሰቡ፤ ኢየሱስንም በሸንጓቸው ፊት አቀረቡት።


አይሁድም ኢየሱስን ከቀያፋ ወደ ሮማዊው ገዥ ግቢ ይዘውት ሄዱ፤ ጊዜውም ማለዳ ነበር። አይሁድም ፋሲካን መብላት እንዲችሉ፣ ላለመርከስ ወደ ገዥው ግቢ አልገቡም።


ነገር ግን የጦር አዛዡ ሉስዮስ መጥቶ በታላቅ ኀይል ከእጃችን ነጥቆ ወሰደው፤ ከሳሾቹም ወደ አንተ እንዲመጡ አዘዘ።]


ዐይናቸው ቅንዝር የተሞላ በመሆኑ ኀጢአትን ከመሥራት አይቈጠቡም፤ ጽኑ ያልሆኑትን ነፍሳት ያስታሉ፤ ሥሥትን የለመደ ልብ አላቸው፤ የተረገሙ ናቸው!


跟着我们:

广告


广告