21 በረዶ ቢጥል ለቤተ ሰዎቿ አትሠጋም፤ ሁሉም ቀይ ልብስ ለብሰዋልና።
21 ለቤትዋ ሰዎች ብርድን አትፈራም፥ የቤትዋ ሰዎች ሁሉ እጥፍ ድርብ የለበሱ ናቸውና።
21 ቤተሰብዋ በሙሉ ሞቃት ልብስ ስላለው በረዶ እንኳ ቢዘንብ አትሠጋም።
ለእያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት የክት ልብስ ሰጣቸው፤ ለብንያም ግን ሦስት መቶ ጥሬ ብርና ዐምስት የክት ልብስ ሰጠው።
“እናንተ የእስራኤል ቈነጃጅት ሆይ፤ ሐምራዊ ቀሚስና ቀጭን ፈትል ላለበሳችሁ፣ ልብሶቻችሁንም በወርቀ ዘቦ ላስጌጠላችሁ፣ ለሳኦል አልቅሱለት።
ላዘነ ልብ የሚዘምር፣ በብርድ ቀን ልብሱን እንደሚያወልቅ፣ ወይም በሶዳ ላይ እንደ ተጨመረ ሖምጣጤ ነው።
ለመኝታዋ የዐልጋ ልብስ ትሠራለች፤ ቀጭን በፍታና ሐምራዊ ልብስ ለብሳለች።
ሠረገሎች በአደባባይ ወዲያ ወዲህ ይከንፋሉ፤ በመንገዶችም ላይ ይርመሰመሳሉ፤ የሚንበለበል ፋና ይመስላሉ፤ እንደ መብረቅም ይወረወራሉ።