14 እንደ ንግድ መርከብ፣ ምግቧን ከሩቅ ትሰበስባለች።
14 እርሷ እንደ ነጋዴ መርከብ ናት፥ ከሩቅ አገር ምግብዋን ትሰበስባለች።
14 እንደ ነጋዴ መርከብ ወደ ሩቅ ስፍራዎች በመሄድ ልዩ ልዩ ዐይነት ምግቦችን ትሰበስባለች።
የኪራም ሰዎችና የሰሎሞን ሰዎች ከኦፊር ወርቅ እንደዚሁም ሰንደልና የከበሩ ድንጋዮች አመጡ።
የበግ ጠጕርና የተልባ እግር መርጣ፣ ሥራ በሚወድዱ እጆቿ ትፈትላቸዋለች።
የበፍታ መጐናጸፊያዎችን ሠርታ ትሸጣለች፤ ለነጋዴዎችም ድግ ታቀርባለች።
የቤተ ሰቦቿን ጕዳይ በትጋት ትከታተላለች፤ የስንፍና እንጀራ አትበላም።