12 በሕይወት ዘመኗ ሁሉ፣ መልካም ታደርግለታለች እንጂ አትጐዳውም።
12 ዕድሜዋን ሙሉ መልካም ታደርግለታለች፥ ክፉም አታደርግም።
12 በምትኖርበት ዘመን ሁሉ መልካም ነገር ታደርግለታለች እንጂ ክፉ ነገር አታደርግበትም።
ባሏ ሙሉ በሙሉ ይተማመንባታል፤ የሚጐድልበትም ነገር የለም።
የበግ ጠጕርና የተልባ እግር መርጣ፣ ሥራ በሚወድዱ እጆቿ ትፈትላቸዋለች።