Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 27:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የራስህንም ሆነ የአባትህን ወዳጅ አትተው፤ መከራ በሚያጋጥምህ ጊዜ ወደ ወንድምህ ቤት አትሂድ፤ ሩቅ ካለ ወንድም ቅርብ ያለ ጎረቤት ይሻላል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ወዳጅህንና የአባትህን ወዳጅ አትተው፥ በመከራህም ቀን ወደ ወንድምህ ቤት አትግባ፥ የቀረበ ወዳጅ ከራቀ ወንድም ይሻላል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ወዳጆችህን ወይም የአባትህን ወዳጆች አትርሳ፤ ችግር ሲደርስብህ የወንድምህን ርዳታ አትጠይቅ፤ ከሩቅ ካለ ወንድም ይልቅ በቅርብ ያለ ጐረቤት ይጠቅምሃል።

参见章节 复制




ምሳሌ 27:10
17 交叉引用  

የሳኦል ልጅ ሜምፊቦስቴም ንጉሡን ለመቀበል ወረደ። ንጉሡ ከተሰደደበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ተመለሰበት ዕለት ድረስ ለእግሩ ተገቢውን ጥንቃቄ አላደረገም፤ ጢሙን አልተላጨም፤ ልብሱንም አላጠበም ነበር።


የአባቴ ቤት ሁሉ ከንጉሥ ጌታዬ ሞት እንጂ ሌላ የሚገባው አልነበረም፤ አንተ ግን ባሪያህን በማእድህ ከሚካፈሉት ጋራ አስቀመጥኸው፤ ከዚህ በላይ ይደረግልኝ ብዬ ንጉሡን ለመጠየቅ ምን መብት አለኝ?”


ንጉሥ ዳዊት በራሱና በሳኦል ልጅ በዮናታን መካከል በእግዚአብሔር ፊት ስላደረጉት መሐላ ሲል የሳኦልን ልጅ፣ የዮናታንን ልጅ ሜምፊቦስቴን ከሞት አተረፈ።


ንጉሥ ኢዮአስ የዘካርያስ አባት ዮዳሄ ያደረገለትን ቸርነት አላሰበም፤ በዚህ ፈንታ ልጁን ገደለው፤ በሚሞትበትም ጊዜ፣ “እግዚአብሔር ይየው፤ እርሱው ይበቀልህ” አለ።


ወዳጅ ምን ጊዜም ወዳጅ ነው፤ ወንድምም ለክፉ ቀን ይወለዳል።


ወዳጅ የሚያበዛ ሰው ራሱን ለጥፋት ይዳርጋል፤ ነገር ግን ከወንድም አብልጦ የሚቀርብ ጓደኛም አለ።


ድኻ በሥጋ ዘመዶቹ ሁሉ የተጠላ ነው፤ ታዲያ ወዳጆቹማ የቱን ያህል ይሸሹት! እየተከታተለ ቢለማመጣቸውም፣ ከቶ አያገኛቸውም።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አባቶቻችሁ ከእኔ የራቁት፣ ከንቱ ነገርን የተከተሉት፣ ራሳቸውም ከንቱ የሆኑት፣ ምን ጥፋት አግኝተውብኝ ነው?


በነጋም ጊዜ፣ አይሁድ ተሰብስበው በማሤር ጳውሎስን እስኪገድሉ ድረስ እህል ውሃ ላለመቅመስ ተማማሉ። በዚህ ሤራ


የወንድምህ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ሲባዝን ብታየው፣ ወደ እርሱ መልሰህ አምጣለት እንጂ ዝም ብለህ አትለፈው፤


跟着我们:

广告


广告