18 ትንታግ ወይም የሚገድል ፍላጻ እንደሚወረውር እብድ፣
18 ትንታግንና ፍላጻን ሞትንም እንደሚወረውር እንደ ዕብድ ሰው፥
18-19 ሰውን አታሎ “በቀልድ ነው ያደረግኹት” የሚል ሰው በአደገኛ የጦር መሣሪያ እንደሚጫወት ዕብድ ሰው ነው።
ቀስተኞች በጭካኔ አጠቁት፤ በጥላቻም ነደፉት።
በባልንጀራው ላይ በሐሰት የሚመሰክር፣ እንደ ቈመጥ፣ እንደ ሰይፍና እንደ ተሳለ ፍላጻ ነው።
ፍላጻ ጕበቱን እስኪወጋው ድረስ፣ ሕይወቱን እንደሚያሳጣው ሳያውቅ፣ በርራ ወደ ወጥመድ እንደምትገባ ወፍ ሆነ።
አሁን ግን እናንተ እሳት አንድዳችሁ፣ የራሳችሁን የሚንቦገቦግ ችቦ የያዛችሁ ሁሉ፣ በሉ በእሳታችሁ ብርሃን ሂዱ፤ ባንቦገቦጋችሁትም የችቦ ብርሃን ተመላለሱ። እንግዲህ ከእጄ የምትቀበሉት ይህ ነው፤ በሥቃይም ትጋደማላችሁ።
ከዚያም ወጥቶ በመሄድ ሦስት መቶ ቀበሮች ያዘ፤ የሁለት ሁለቱን ጭራ አንድ ላይ ካሰረ በኋላ ችቦ ወስዶ ጥንድ ሆኖ ከተያያዘው ጭራ ጋራ አሰረው።