Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 17:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ጠብ የሚወድድ ኀጢአትን ይወድዳል፤ በሩን ከፍ አድርጎ የሚሠራም ጥፋትን ይጋብዛል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ዓመፃን የሚወድድ ክርክርን ይወድዳል፥ ደጁንም ዘለግ የሚያደርግ ውድቀትን ይሻል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ኃጢአትን የሚወድ ጠብን ይወዳል፤ ከፍ ብሎ እንደ ተሠራ ደጃፍ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ሰው ውድቀትን ይጋብዛል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ክርክርን የሚወድድ በጠብ ደስ ይለዋል።

参见章节 复制




ምሳሌ 17:19
14 交叉引用  

ከዚህ በኋላ አቤሴሎም ሠረገላና ፈረሶች እንዲሁም ፊት ፊቱ የሚሮጡ ዐምሳ ሰዎች ለራሱ አዘጋጀ።


በዚህ ጊዜ ከአጊት የተወለደው አዶንያስ፣ “እነግሣለሁ” ብሎ ተነሣ፤ ስለዚህ ሠረገሎችንና ፈረሶችን እንዲሁም ከፊት ከፊቱ የሚሄዱ ዐምሳ ሰዎችን አዘጋጀ።


ትዕቢት ጥፋትን፣ የእብሪት መንፈስም ውድቀትን ትቀድማለች።


ጠብ መጫር ግድብን እንደ መሸንቈር ነው፤ ስለዚህ ጠብ ከመጫሩ በፊት ከነገር ራቅ።


ከውድቀቱ በፊት ሰው ልቡ ይታበያል፤ ትሕትና ግን ክብርን ትቀድማለች።


በደጅ ያለውን ሥራህን ፈጽም፤ ዕርሻህን አዘጋጅ፤ ከዚያም በኋላ ቤትህን ሥራ።


ጠቢብ ሰው ከቂል ጋራ ወደ ሸንጎ ቢሄድ፣ ቂሉ ይቈጣል፤ ያፌዛል፤ ሰላምም አይኖርም።


ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ፣ እኔ እንደምፈልገው ሆናችሁ ላላገኛችሁ እችላለሁ ወይም እናንተ እንደምትፈልጉኝ ሆኜ ላታገኙኝ ትችላላችሁ ብዬ እፈራለሁ፤ ምናልባትም በመካከላችሁ ጥል፣ ቅናት፣ ቍጣ፣ አድመኝነት፣ ስም ማጥፋት፣ ሐሜት፣ እብሪትና ሁከት ይኖራል ብዬ እሠጋለሁ።


የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያመጣምና።


跟着我们:

广告


广告