Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 12:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ትጉህ እጆች ለገዥነት ሲያበቁ፣ የስንፍና ፍጻሜ ግን የባርነት ሥራ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 የትጉ እጅ ትገዛለች፥ የታካች እጅ ግን ትገብራለች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 በሥራ ትጉህ መሆን ገዢ ያደርጋል፤ ሰነፍ መሆን ግን ተገዢ ያደርጋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 የተመረጡ ሰዎች እጅ ፈጥኖ ይገዛል፤ ሐሰተኞች ሰዎች ግን ለምርኮ ይሆናሉ።

参见章节 复制




ምሳሌ 12:24
15 交叉引用  

ማረፊያ ቦታው መልካም፣ ምድሪቱም አስደሳች መሆኗን ሲያይ፣ ትከሻውን ለሸክም ያመቻቻል፤ ተገድዶም ያገለግላል።


ኢዮርብዓም ከፍተኛ ችሎታ ያለው ሰው ነበር፤ ሰሎሞንም ወጣቱ ሥራውን እንዴት በሚገባ እንደሚያከናውን ባየ ጊዜ፣ በዮሴፍ ነገድ ለሚሠራው የጕልበት ሥራ ሁሉ ሾመው።


ኢዮርብዓም መመለሱን እስራኤላውያን ሁሉ በሰሙ ጊዜ፣ ወደ ጉባኤያቸው በማስጠራት በመላው እስራኤል ላይ አነገሡት። ለዳዊት ቤት በታማኝነት ጸንቶ የተገኘው የይሁዳ ቤት ብቻ ነው።


እስራኤላውያን ዘሮቻቸውን ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት ያልቻሉትንና በምድሪቱ የቀሩትን የእነዚህን ሕዝቦች ዘሮች እስከ ዛሬ ድረስ እንደሚደረገው የጕልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ ሰሎሞን መለመላቸው።


ሰነፍ እጆች ሰውን ያደኸያሉ፤ ትጉህ እጆች ግን ብልጽግናን ያመጣሉ።


ሰነፍ ዐድኖ ያመጣውን እንኳ አይጠብስም፤ ትጉህ ሰው ግን ለንብረቱ ዋጋ ይሰጣል።


ሰነፍ አጥብቆ ይመኛል፤ አንዳችም አያገኝም፤ የትጉሆች ምኞት ግን ይረካል።


ጠቢብ አገልጋይ በወራዳ ልጅ ላይ ሥልጣን ይኖረዋል፤ ከወንድማማቾቹም እንደ አንዱ ውርስ ይካፈላል።


ስንፍና ከባድ እንቅልፍ ላይ ይጥላል፤ ዋልጌም ሰው ይራባል።


ሰነፍ፣ “አንበሳ በውጭ አለ፤ በጐዳና ላይ እገደላለሁ” ይላል።


በሙያው ሥልጡን የሆነውን ሰው አይተሃልን? በነገሥታት ዘንድ ባለሟል ይሆናል፤ አልባሌ ሰዎችን አያገለግልም።


እስራኤላውያን በበረቱ ጊዜ ግን ከነዓናውያንን የጕልበት ሥራ እንዲሠሩ አስገደዷቸው እንጂ ፈጽሞ አላስወጧቸውም።


跟着我们:

广告


广告