Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 12:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 መሬቱን የሚያርስ የተትረፈረፈ ምግብ ያገኛል፤ ከንቱ ተስፋን የሚያሳድድ ግን ልበ ቢስ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 መሬቱን የሚቆፍር ሰው እንጀራ ይጠግባል፥ ለከንቱ ነገር የሚሮጥ ግን ማስተዋል የተሣነው ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ትጉህ ገበሬ የተትረፈረፈ ምግብ ይኖረዋል፤ በከንቱ ምኞት መጠመድ ግን ሞኝነት ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ምድሩን የሚያርሳት ሰው እንጀራን ይጠግባል፤ ቦዘኔነትን የሚከተል ግን የአእምሮ ድህነትን ይሰበስባል። በወይን ግብዣ ራሱን ደስ የሚያሰኝ ሰው በሰውነቱ ውርደትን ያመጣል።

参见章节 复制




ምሳሌ 12:11
23 交叉引用  

ከምድር ስለ ተገኘህ፣ ወደ መጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ እንጀራህን በፊትህ ላብ ትበላለህ፤ ዐፈር ነህና ወደ ዐፈር ትመለሳለህ።”


የድካምህን ፍሬ ትበላለህ፤ ብፅዕና እና ብልጽግና የአንተ ይሆናሉ።


ከማይረቡ ጋራ አልተቀመጥሁም፤ ከግብዞችም ጋራ አልተባበርሁም።


ከጠቢብ ጋራ የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤ የሞኝ ባልንጀራ ግን ጕዳት ያገኘዋል።


የድኾች ዕርሻ የተትረፈረፈ ምርት ያስገኛል፤ የፍትሕ መጓደል ግን ጠራርጎ ይወስደዋል።


ለፍተው የሠሩት ሁሉ ትርፍ ያስገኛል፤ ከንቱ ወሬ ግን ወደ ድኽነት ያመራል።


በሬዎች በሌሉበት በረቱ ባዶ ይሆናል፤ በበሬ ጕልበት ግን ብዙ ምርት ይገኛል።


እንቅልፍ አትውደድ፤ አለዚያ ድኻ ትሆናለህ፤ ዐይንህን ክፈት፤ የተትረፈረፈ ምግብ ይኖርሃል።


አንተንና ቤተ ሰብህን፣ ገረዶችህንም ጭምር ለመመገብ፣ የተትረፈረፈ የፍየል ወተት ይኖርሃል።


መሬቱን የሚያርስ የተትረፈረፈ ምግብ ያገኛል፤ ከንቱ ተስፋን ይዞ የሚጓዝ ግን በድኽነት ይሞላል።


የሚያመነዝር ሰው ግን ልበ ቢስ ነው፤ እንዲህ የሚያደርግ ሁሉ ራሱን ያጠፋል።


ልበ ቢሱን ወጣት፣ ከአላዋቂዎች መካከል አየሁት፤ ከጕልማሶችም መካከል ለየሁት።


ጥበብ የለሽ ሴት ለፍላፊ ናት፤ እርሷም ስድና ዕውቀት የለሽ ናት።


እርሷም ልበ ቢሶችን፣ “አላዋቂዎች ሁሉ ወደዚህ ኑ” ትላለች።


የአላዋቂነት መንገዳችሁን ተዉ፤ በሕይወት ትኖራላችሁ፤ በማስተዋልም መንገድ ተመላለሱ።”


“ከንቱ በሆኑ ጣዖቶች ላይ የሚንጠለጠሉ፣ ሊያገኙ የሚገባቸውን ጸጋ ያጣሉ።


ይሰርቅ የነበረ ከእንግዲህ አይስረቅ፤ ነገር ግን ለተቸገሩት የሚያካፍለው ነገር እንዲኖረው በገዛ እጆቹ በጎ የሆነውን እየሠራ ለማግኘት ይድከም።


ደግሞም የማንንም እንጀራ በነጻ አልበላንም፤ ነገር ግን ከእናንተ በአንዳችሁም ላይ ሸክም እንዳንሆን ሌሊትና ቀን እንደክምና እንሠራ ነበር፤


እነርሱም በኣልብሪት ቤተ ጣዖት ሰባ ሰቅል ብር ሰጡት፤ አቢሜሌክም በዚያ ወሮበሎችንና ምናምንቴዎችን ቀጠረበት፤ እነርሱም ተከተሉት።


跟着我们:

广告


广告