Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 11:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 በሀብቱ የሚታመን ሁሉ ይወድቃል፤ ጻድቃን ግን እንደ አረንጓዴ ቅጠል ይለመልማሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 በባለጠግነቱ የሚተማመን ሰው ይወድቃል፥ ጻድቃን ግን እንደ ቅጠል ይለመልማሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 በሀብታቸው የሚተማመኑ ሰዎች እንደ ቅጠል ይረግፋሉ፤ እውነተኞች ሰዎች ግን እንደ መልካም ተክል ይለመልማሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 በባለጠግነቱ የሚተማመን ሰው ይወድቃል፤ ጻድቃንን የሚቀበል ግን ይለመልማል።

参见章节 复制




ምሳሌ 11:28
13 交叉引用  

እርሱም በወራጅ ውሃ ዳር እንደ ተተከለች፣ ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፣ ቅጠሏም እንደማይጠወልግ ዛፍ ነው፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።


በሀብታቸው የሚመኩትን፣ በብልጽግናቸውም የሚታመኑትን ለምን እፈራለሁ?


በዝርፊያ አትታመኑ፤ በቅሚያም ተስፋ አታድርጉ፤ በዚህ ብትበለጽጉም፣ ልባችሁ ይህን አለኝታ አያድርግ።


የባለጠጎች ሀብት የተመሸገ ከተማቸው ነው፤ ድኽነት ግን የድኾች መጥፊያ ናት።


ሕዝብሽም ሁሉ ጻድቃን ይሆናሉ፤ ምድሪቱንም ለዘላለም ይወርሳሉ፤ ለክብሬ መግለጫ ይሆኑ ዘንድ፣ የእጆቼ ሥራ፣ እኔ የተከልኋቸው ቍጥቋጦች ናቸው።


በውሃ ዳር እንደ ተተከለ፣ ሥሩንም ወደ ወንዝ እንደ ሰደደ ዛፍ ነው፣ ሙቀት ሲመጣ አይፈራም፤ ቅጠሉም ዘወትር እንደ ለመለመ ነው፤ በድርቅ ዘመን አይሠጋም፤ ፍሬ ማፍራቱንም አያቋርጥም።”


“እግዚአብሔር ግን፣ ‘አንተ ሞኝ፤ ነፍስህን በዚህች ሌሊት ከአንተ ሊወስዱ ይፈልጓታል፤ እንግዲህ፣ ለራስህ ያከማቸኸው ለማን ይሆናል?’ አለው።


በዚህ ዓለም ባለጠጎች የሆኑት እንዳይታበዩ፣ ደስም እንዲለን ሁሉን ነገር አትረፍርፎ በሚሰጠን በእግዚአብሔር እንጂ አስተማማኝነት በሌለው በሀብት ላይ ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።


跟着我们:

广告


广告