Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ፊልጵስዩስ 4:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከዚህም በላይ፣ እናንተ የፊልጵስዩስ ሰዎች ራሳችሁ እንደምታውቁት፣ በመጀመሪያ ወንጌልን በተቀበላችሁ ጊዜ ከመቄዶንያ ስነሣ፣ ከእናንተ በቀር በመስጠትና በመቀበል የትኛውም ቤተ ክርስቲያን አልተባበረኝም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የፊልጵስዩስ ሰዎች ሆይ! ወንጌል በመጀመሪያ ሲሰበክ፥ ከመቄዶንያ በወጣሁ ጊዜ፥ ከእናንተ ብቻ በቀር ሌላ ቤተ ክርስቲያን በመስጠትና በመቀበል ስሌት ከእኔ ጋር እንዳልተባበረ እናንተ ደግሞ ታውቃላችሁ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ከዚህም በቀር ወንጌልን ለማብሠር በጀመርኩበት ጊዜ ከመቄዶንያ ስወጣ ከእናንተ በፊልጵስዩስ ከምትገኙት አማኞች በቀር በመስጠትም ሆነ በመቀበል ከእኔ ጋር የተባበረ ሌላ ማኅበረ ምእመናን እንዳልነበረ እናንተው ራሳችሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እና​ንተ የፊ​ል​ጵ​ስ​ዩስ ሰዎች፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ትም​ህ​ርት ከመ​ቄ​ዶ​ንያ ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ፥ ከእ​ና​ንተ ብቻ በቀር ሌላ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በመ​ስ​ጠ​ትም ቢሆን፥ በመ​ቀ​በል ከእኔ ጋር እን​ዳ​ል​ተ​ባ​በሩ እና​ንተ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የፊልጵስዩስ ሰዎች ሆይ፥ ወንጌል በመጀመሪያ ሲሰበክ፥ ከመቄዶንያ በወጣሁ ጊዜ፥ ከእናንተ ብቻ በቀር ሌላ ቤተ ክርስቲያን በመስጠትና በመቀበል ስሌት ከእኔ ጋር እንዳልተካፈለች እናንተ ደግሞ ታውቃላችሁ፤

参见章节 复制




ፊልጵስዩስ 4:15
12 交叉引用  

ነቢዩም፣ “የማገለግለውን ሕያው እግዚአብሔርን፣ ምንም ነገር አልቀበልም” ሲል መለሰ። ምንም እንኳ ንዕማን አስጨንቆ ቢለምነውም አልተቀበለም።


የእግዚአብሔር ሰው የኤልሳዕ አገልጋይ ግያዝ፣ “ጌታዬ፤ ይህ ሶርያዊ ንዕማን ያመጣውን አለመቀበሉ አይደል፤ ሕያው እግዚአብሔርን! ተከትዬ ሄጄ ከርሱ አንድ ነገር ማግኘት አለብኝ” ብሎ ዐሰበ።


ጳውሎስና ሲላስ ከእስር ቤቱ ከወጡ በኋላ ወደ ልድያ ቤት ሄዱ፤ በዚያም ወንድሞችን አግኝተው አበረታቷችው፤ ከዚያም በኋላ ሄዱ።


ምክንያቱም መቄዶንያና አካይያ፣ በኢየሩሳሌም ካሉት ቅዱሳን መካከል የሚገኙትን ድኾች ለመርዳት ተነሣሥተዋልና።


አሁንም ወንድሞች ሆይ፣ በእኔ ላይ የደረሰው ነገር ወንጌል በይበልጥ እንዲስፋፋ መርዳቱን ታውቁ ዘንድ እወድዳለሁ።


እነዚህ፣ እኔ ለወንጌል ለመሟገት እዚህ እንዳለሁ ስለሚያውቁ፣ በፍቅር ይህን ያደርጋሉ፤


ከመጀመሪያው ቀን አንሥቶ እስካሁን ድረስ በወንጌል አገልግሎት ተካፋይ ሆናችኋልና።


በልቤ ስላላችሁ እና በእስራቴም ሆነ ለወንጌል ስመክትና ሳጸናው ሁላችሁም ከእኔ ጋራ የእግዚአብሔር ጸጋ ተካፋዮች ስለ ሆናችሁ፣ ስለ ሁላችሁ እንዲህ ማሰቤ ተገቢ ነው።


ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ፤ ሁልጊዜም ታዛዦች እንደ ነበራችሁ ሁሉ፣ አሁንም እኔ በአጠገባችሁ ሳለሁ ብቻ ሳይሆን፣ ይልቁንም አሁን በሌለሁበት ጊዜ በፍርሀትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤


跟着我们:

广告


广告