Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አብድዩ 1:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 አንተ በሰንጣቃ ዐለት ውስጥ የምትኖር፣ መኖሪያህንም በከፍታ ስፍራ ያደረግህ፣ ለራስህም፣ ‘ማን ወደ ምድር ሊያወርደኝ ይችላል?’ የምትል፣ የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ የምትኖር፥ ማደሪያህንም ከፍ ከፍ ያደረግህ፥ በልብህም፦ ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው? የምትል አንተ ሆይ፥ የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የልብህ ትዕቢት አታሎሃል፤ በጠንካራ አለት በተመሸገ ከተማ ውስጥ ትኖራለህ፤ የምታድርበትም ቤት በከፍተኞች ተራራዎች ላይ የተሠራ ነው፤ ‘ካለሁበት ስፍራ ማን ሊያወርደኝ ይችላል?’ በማለት ትመካለህ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በተ​ሰ​ነ​ጠ​ቀም ዓለት ውስጥ እን​ደ​ሚ​ኖር- ማደ​ሪ​ያ​ው​ንም ከፍ ከፍ እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በል​ቡም፦ ወደ ምድር የሚ​ያ​ወ​ር​ደኝ ማን ነው? እን​ደ​ሚል፥ የል​ብህ ትዕ​ቢት እጅግ አኵ​ር​ቶ​ሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ የምትኖር፥ ማደሪያህንም ከፍ ከፍ ያደረግህ፥ በልብህም፦ ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው? የምትል አንተ ሆይ፥ የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል።

参见章节 复制




አብድዩ 1:3
21 交叉引用  

ስለዚህ ኤዶም የተባለው ዔሳው መኖሪያውን በተራራማው አገር በሴይር አደረገ።


የጨው ሸለቆ በተባለው ቦታ ዐሥር ሺሕ ኤዶማውያንን ድል ያደረገ፣ ሴላን በጦርነት የያዘና እስከ ዛሬም ድረስ ዮቅትኤል ተብላ የምትጠራበትን ስም ያወጣላት አሜስያስ ነው።


አሜስያስም ኀይሉን በሚገባ አደራጅቶ ሰራዊቱን ወደ ጨው ሸለቆ መራ፤ በዚያም ዐሥር ሺሕ የሴይር ወታደሮችን ገደለ።


የይሁዳ ሰራዊት ሌሎች ዐሥር ሺሕ ሰዎች ማረኩ፤ ወደ አንድ ዐለት ዐናት ላይም አውጥተው ቍልቍል ለቀቋቸው፤ ሁሉም ተፈጠፈጡ።


እስከ ሰማይ ከፍ ከፍ ቢልም፣ ዐናቱም ደመናትን ቢነካ፣


ትዕቢት ጥፋትን፣ የእብሪት መንፈስም ውድቀትን ትቀድማለች።


ከውድቀቱ በፊት ሰው ልቡ ይታበያል፤ ትሕትና ግን ክብርን ትቀድማለች።


ሰውን ትዕቢቱ ያዋርደዋል፤ ትሑት መንፈስ ያለው ግን ክብርን ይጐናጸፋል።


የሞዓብን መዘባነን፣ እጅግ መታበዩንና ኵራቱን፣ እብሪቱንና ስድነቱን ሰምተናል፤ ትምክሕቱ ግን ከንቱ ነው!


ከሸለቆው በላይ፣ በድንጋያማው ዐምባ ላይ የምትኖሪ ሆይ፤ እኔ በአንቺ ላይ ወጥቻለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር። “ማን በእኛ ላይ ይወጣል? ማንስ ወደ መኖሪያችን ደፍሮ ይገባል?” የምትሉ ሆይ፤


“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ባቢሎናውያን በርግጥ ትተውን ይሄዳሉ’ ብላችሁ አታስቡ፤ አይሄዱምና ራሳችሁን አታታልሉ።


እናንተ በሞዓብ የምትኖሩ ሆይ፤ ከከተማ ወጥታችሁ በዐለት መካከል ኑሩ፤ በገደል አፋፍ ላይ ጐጆዋን እንደምትሠራ፣ እንደ ርግብ ሁኑ።


አንተ በዐለት ንቃቃት ውስጥ የምትኖር፣ የተራራውንም ከፍታ የያዝህ ሆይ፤ የምትነዛው ሽብር፣ የልብህም ኵራት አታልሎሃል፤ መኖሪያህን እስከ ንስር ከፍታ ቦታ ብትሠራም፣ ከዚያ ወደ ታች አወርድሃለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር።


አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ፤ በሸለቆችሽ ለምን ትመኪያለሽ? ለምንስ በፍሬያማ ሸለቆሽ ትኵራሪያለሽ? በብልጽግናሽ ተማምነሽ፣ ‘ማን ሊነካኝ ይችላል?’ ትያለሽ።


ንግድህ ስለ ደረጀ፣ በዐመፅ ተሞላህ፣ ኀጢአትም ሠራህ፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ተራራ በውርደት አሳደድሁህ፤ ጠባቂ ኪሩብ ሆይ፤ ከእሳት ድንጋዮች መካከል አስወጣሁህ።


ኤዶምያስ፣ “ብንደመሰስም እንኳ የፈረሰውን መልሰን እንሠራዋለን” ይል ይሆናል። የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፤ “እነርሱ ይሠሩ ይሆናል፤ እኔ ግን አፈርስባቸዋለሁ፤ ክፉ ምድር፣ እግዚአብሔርም ለዘላለም የተቈጣው ሕዝብ ተብለው ይጠራሉ።


跟着我们:

广告


广告