Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አብድዩ 1:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ስደተኞቻቸውን ለመግደል፣ በመንታ መንገድ መጠባበቅ አይገባህም ነበር፤ በጭንቀታቸው ቀን፣ የተረፉትን አሳልፈህ መስጠት አልነበረብህም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የሸሹትንም ለመግደል በመንታ መንገድ ላይ ልትቆም፥ በጭንቀትም ቀን ከእርሱ የቀሩትን አሳልፈህ ልትሰጥ አይገባህም ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የሚሸሹትን ለመግደል በመስቀልኛ መንገድ ላይ ባላደባህባቸውም ነበር፤ የተረፉትንም በመከራቸው ቀን ለጠላት አሳልፈህ መስጠት ባልተገባህም ነበር።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የሸ​ሹ​ት​ንም ለማ​ጥ​ፋት በመ​ተ​ላ​ለ​ፊያ መን​ገ​ዳ​ቸው ትቆም ዘንድ፥ ድል በተ​ነ​ሡ​በ​ትም ቀን ከእ​ርሱ ያመ​ለ​ጡ​ትን ለማ​ስ​ጨ​ነቅ ትከ​ብ​ባ​ቸው ዘንድ ባል​ተ​ገ​ባህ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የሸሹትንም ለመግደል በመንታ መንገድ ላይ ትቆም ዘንድ፥ በጭንቀትም ቀን ከእርሱ የቀሩትን አሳልፈህ ትሰጥ ዘንድ አይገባህም ነበር።

参见章节 复制




አብድዩ 1:14
10 交叉引用  

ተነሥተን ወደ ቤቴል እንውጣ፤ እዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ፣ በሄድሁበትም ስፍራ ሁሉ ላልተለየኝ አምላክ መሠዊያ እሠራለሁ።”


ለጠላት አሳልፈህ አልሰጠኸኝም፤ ነገር ግን እግሮቼን ሰፊ ቦታ ላይ አቆምሃቸው።


“ምክር ለግሱን፤ ውሳኔ ስጡን፤ በቀትር ጥላችሁን እንደ ሌሊት አጥሉብን፤ የሸሹትን ደብቁ፤ ስደተኞችን አሳልፋችሁ አትስጡ።


የሞዓባውያን ስደተኞች ከእናንተ ጋራ ይቈዩ፤ እናንተም ከአጥፊው መጠጊያ ሁኗቸው።” የጨቋኙ ፍጻሜ ይመጣል፤ ጥፋቱ ያከትማል፤ እብሪተኛም ከምድር ገጽ ይጠፋል።


እነርሱም እንዲህ አሉት፤ “ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፤ ‘ይህ ቀን የጭንቀት፣ የተግሣጽና የውርደት ቀን ነው፤ ልጆች ሊወለዱ ሲሉ ብርታት እንደሚታጣበት ቀን ሆኗል።


ወዮ ለዚያ ቀን! እንደዚያም ያለ አይኖርም፤ ለያዕቆብ የመከራ ጊዜ ነው፤ ነገር ግን ይተርፋል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የጋዛ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤ ሕዝቡን ሁሉ ማርካ በመውሰድ፣ ለኤዶም ሸጣለችና።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የጢሮስ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም። የወንድማማችነትን ቃል ኪዳን በማፍረስ፣ ሕዝቡን ሁሉ ማርካ ለኤዶም ሸጣለችና።


ክፉ ቀን በገጠመው ጊዜ፣ በወንድምህ ሥቃይ መደሰት አልነበረብህም፤ በጥፋታቸው ቀን፣ የይሁዳ ሕዝብ ሲያዝኑ ሐሤት ማድረግ አልነበረብህም፤ በጭንቀታቸውም ቀን፣ በትዕቢት ልትናገር አይገባህም ነበር።


ወደ መንገድ መተላለፊያ ወጥታችሁ ያገኛችሁትን ሁሉ ወደ ሰርጉ ድግስ ጥሩ።’


跟着我们:

广告


广告