ዘኍል 7:88 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም88 ለኅብረት መሥዋዕት የቀረቡት እንስሳት ድምር ሃያ አራት በሬ፣ ስድሳ አውራ በግ፣ ስድሳ ተባዕት ፍየልና ስድሳ አንድ ዓመት የሆናቸው ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበር። እንግዲህ መሠዊያው ከተቀባ በኋላ ለመሠዊያው መቀደስ የቀረቡ ስጦታዎች እነዚህ ናቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)88 የአንድነትም መሥዋዕት ከብት ሁሉ ሀያ አራት በሬዎች፥ ስልሳም አውራ በጎች፥ ስልሳም አውራ ፍየሎች፥ ስልሳም የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። መሠዊያው ከተቀባ በኋላ መሠዊያውን ለመቀደስ የቀረበ መባ ይህ ነበረ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም88 ለአንድነት መሥዋዕት የቀረቡት የከብት ብዛት፦ ኻያ አራት ኰርማዎች፥ ሥልሳ አውራ በጎች፥ ሥልሳ ተባት ፍየሎች፥ ባለ አንድ ዓመት ዕድሜ ሥልሳ ተባት በጎች፥ መሠዊያው ከተቀባ በኋላ ለመቅደስ የቀረበ ቊርባን ይህ ነው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)88 የደኅንነትም መሥዋዕት ከብት ሁሉ፥ ሃያ አራት ጊደሮች፥ ስድሳም አውራ በጎች፥ ስድሳም አውራ ፍየሎች፥ ስድሳም ነውር የሌለባቸው የአንድ ዓመት እንስት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። መሠዊያው ከተቀባ በኋላ ለመቀደሻው የቀረበ ቍርባን ይህ ነበረ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)88 የደኅንነትም መሥዋዕት ከብት ሁሉ ሀያ አራት በሬዎች፥ ስድሳም አውራ በጎች፥ ስድሳም አውራ ፍየሎች፥ ስድሳም የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። መሠዊያው ከተቀባ በኋላ ለመቀደሻው የቀረበ ቍርባን ይህ ነበረ። 参见章节 |